መጽሐፈ ምሳሌ 5
5
1ልጄ ሆይ፥ ጥበቤን አድምጥ፥
ጆሮህን ወደ ትምህርቴ አዘንብል፥
2ጥንቃቄን ትጠብቅ ዘንድ
ከንፈሮችህም እውቀትን እንዲጠብቁ።
3ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥
አፍዋም ከዘይት የለዘበ ነውና፥
4ፍጻሜዋ ግን እንደ እሬት የመረረ ነው፥
ሁለት አፍ እንዳለው ሰይፍም፥ የተሳለ ነው።
5እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ፥
አረማመድዋም ወደ ሲኦል ነው፥
6የቀና የሕይወትን መንገድ አታገኝም፥
በአካሄድዋ የተቅበዘበዘች ናት፥ የሚታወቅም አይደለም።
7አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥
ከአፌም ቃል አትራቁ።
8መንገድህን ከእርሷ አርቅ፥
ወደ ቤትዋም ደጅ አትቅረብ፥
9ክብርህን ለሌላ እንዳትሰጥ፥
ዕድሜህንም ለጨካኝ፥
10ሌሎች ከኃይልህ እንዳይጠግቡ፥
ድካምህም ወደ ባዕድ ሰው ቤት እንዳይሄድ።
11በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ፥
12ትላለህም፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ፥
ልቤም ዘለፋን ናቀ!
13የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፥
ጆሮቼንም ወደ አስተማሪዎቼ አላዘነበልሁም።
14በማኅበርና በጉባኤ መካከል
ለክፉ ሁሉ ለመዳረግ ጥቂት ቀረኝ።”
15ከጉድጓድህ ውኃ፥ ከምንጭህም የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ።
16ምንጮችህ ወደ ሜዳ፥
ወንዞችህ ወደ አደባባይ ይፈስሳሉን?
17ለአንተ ብቻ ይሁኑ፥
ከአንተ ጋር ላሉ እንግዶችም አይሁኑ።
18ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፥
ከጉብዝናህም ሚስት ጋር ደስ ይበልህ።
19እንደ ተወደደች ዋላ እንደ ተዋበችም ሚዳቋ፥
ጡትዋ ሁልጊዜ ታርካህ፥
በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ።
20ልጄ ሆይ፥ ስለምን ጋለሞታ ሴት ትወድዳለህ?
የሌላይቱንስ ብብት ለምን ታቅፋለህ?
21የሰው መንገድ በጌታ ፊት ነውና፥
አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና።
22ክፉ በክፋቱ ይጠመዳል፥
በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።
23አልተቀጣምና እርሱ ይሞታል፥
በአላዊቅነትም ብዛት ይስታል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 5: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ምሳሌ 5
5
1ልጄ ሆይ፥ ጥበቤን አድምጥ፥
ጆሮህን ወደ ትምህርቴ አዘንብል፥
2ጥንቃቄን ትጠብቅ ዘንድ
ከንፈሮችህም እውቀትን እንዲጠብቁ።
3ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥
አፍዋም ከዘይት የለዘበ ነውና፥
4ፍጻሜዋ ግን እንደ እሬት የመረረ ነው፥
ሁለት አፍ እንዳለው ሰይፍም፥ የተሳለ ነው።
5እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ፥
አረማመድዋም ወደ ሲኦል ነው፥
6የቀና የሕይወትን መንገድ አታገኝም፥
በአካሄድዋ የተቅበዘበዘች ናት፥ የሚታወቅም አይደለም።
7አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥
ከአፌም ቃል አትራቁ።
8መንገድህን ከእርሷ አርቅ፥
ወደ ቤትዋም ደጅ አትቅረብ፥
9ክብርህን ለሌላ እንዳትሰጥ፥
ዕድሜህንም ለጨካኝ፥
10ሌሎች ከኃይልህ እንዳይጠግቡ፥
ድካምህም ወደ ባዕድ ሰው ቤት እንዳይሄድ።
11በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ፥
12ትላለህም፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ፥
ልቤም ዘለፋን ናቀ!
13የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፥
ጆሮቼንም ወደ አስተማሪዎቼ አላዘነበልሁም።
14በማኅበርና በጉባኤ መካከል
ለክፉ ሁሉ ለመዳረግ ጥቂት ቀረኝ።”
15ከጉድጓድህ ውኃ፥ ከምንጭህም የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ።
16ምንጮችህ ወደ ሜዳ፥
ወንዞችህ ወደ አደባባይ ይፈስሳሉን?
17ለአንተ ብቻ ይሁኑ፥
ከአንተ ጋር ላሉ እንግዶችም አይሁኑ።
18ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፥
ከጉብዝናህም ሚስት ጋር ደስ ይበልህ።
19እንደ ተወደደች ዋላ እንደ ተዋበችም ሚዳቋ፥
ጡትዋ ሁልጊዜ ታርካህ፥
በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ።
20ልጄ ሆይ፥ ስለምን ጋለሞታ ሴት ትወድዳለህ?
የሌላይቱንስ ብብት ለምን ታቅፋለህ?
21የሰው መንገድ በጌታ ፊት ነውና፥
አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና።
22ክፉ በክፋቱ ይጠመዳል፥
በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።
23አልተቀጣምና እርሱ ይሞታል፥
በአላዊቅነትም ብዛት ይስታል።