መጽሐፈ ምሳሌ 6
6
1 #
ሲራ. 29፥14-20። ልጄ ሆይ፥ ለጎረቤትህ ዋስ ብትሆን፥
ለእንግዳ ሰው ቃል ብትገባ፥
2በአፍህ ቃል ከተጠመድህ፥
በአፍህ ቃል ከተያዝህ።
3ልጄ ሆይ፥ ይህን አድርግ ራስህንም አድን፥
በጎረቤትህ እጅ ወድቀሃልና፥
ፈጥነህ ሂድ፥ ጎረቤትህንም ነዝንዘው።
4ለዓይንህ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶችህም እንጉልቻን አትስጥ፥
5እንደ ሚዳቋ ከአዳኝ እጅ፥
እንደ ወፍም ከአጥማጅ እጅ ትድን ዘንድ።
6አንተ ሰነፍ፥ ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፥
መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን።
7አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት
8መብሏን በበጋ ታሰናዳለች፥
መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች።
9አንተ ሰነፍ፥ እስከ መቼ ትተኛለህ?
ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ?
10 #
ምሳ. 24፥33፤34። ጥቂት መተኛት፥ ጥቂት ማንቀላፋት፥
ለመተኛት ጥቂት እጅን ማጣጠፍ፥
11እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥
ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።
12ከንቱና ክፉ ሰው
ጠማማ ንግግር ይዞ ይዞራል፥
13 #
ሲራ. 27፥22። በዓይኑ ይጠቅሳል፥ በእግሩ ይናገራል፥
በጣቱ ያስተምራል፥
14ጠማማነት በልቡ አለ፥ ሁልጊዜም ክፋትን ያቅዳል፥
ጠብንም ይዘራል።
15ስለዚህ ጥፋት ድንገት ይደርስበታል፥
ድንገት ይደቅቃል፥ ፈውስም ከቶ የለውም።
16ጌታ የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥
ሰባተኛውንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፋቸዋለች፥
17ትዕቢተኛ ዐይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥
ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
18ክፉ አሳብን የሚያቅድ ልብ፥
ወደ ክፉ የሚሮጡ እግሮች፥
19በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
20ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥
የእናትህንም ትምህርት አትተው፥
21ሁልጊዜም በልብህ አኑራቸው፥
በአንገትህም እሰራቸው።
22ስትሄድም ይመሩሃል፥
ስትተኛ ይጠብቁሃል፥
ስትነሣ ያነጋግሩሃል።
23ትእዛዝ መብራት፥ ትምህርትም ብርሃን ነውና፥
የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና፥
24ከክፉ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ
ከሌላይቱም ሴት አታላይ ምላስ።
25ውበትዋን በልብህ አትመኘው፥
በዐይኖችዋም አትማረክ።
26የሴተኛ ዐዳሪዋ ዋጋ እስከ አንዲት እንጀራ ነው፥
አመንዝራም ሴት የሰውን ሕይወት ታጠምዳለች።
27በጉያው እሳትን የሚታቀፍ፥
ልብሶቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው?
28በፍም ላይ የሚሄድ
እግሮቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው?
29ወደ ሰው ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፥
የሚነካትም ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም።
30ሌባ በተራበ ጊዜ ነፍሱን ሊያጠግብ ቢሰርቅ
ሰዎች አይንቁትም፥
31ቢያዝም ሰባት እጥፍ ይከፍላል፥
በቤቱም ያለውን ሁሉ ይሰጣል።
32ከሴት ጋር የሚያመነዝር ግን አእምሮ የጐደለው ነው፥
እንዲሁም የሚያደርግ ነፍሱን ያጠፋል።
33ቁስልንና ውርደትን ያገኛል፥
ስድቡም አይደመሰስም።
34ቅንዓት ለሰው የቁጣ ትኩሳት ነውና፥
በበቀልም ቀን አይራራለትምና።
35እርሱም ምንም ካሣ አይቀበልም፥
ስጦታም ብታበዛለት አይታረቅም።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 6: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ምሳሌ 6
6
1 #
ሲራ. 29፥14-20። ልጄ ሆይ፥ ለጎረቤትህ ዋስ ብትሆን፥
ለእንግዳ ሰው ቃል ብትገባ፥
2በአፍህ ቃል ከተጠመድህ፥
በአፍህ ቃል ከተያዝህ።
3ልጄ ሆይ፥ ይህን አድርግ ራስህንም አድን፥
በጎረቤትህ እጅ ወድቀሃልና፥
ፈጥነህ ሂድ፥ ጎረቤትህንም ነዝንዘው።
4ለዓይንህ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶችህም እንጉልቻን አትስጥ፥
5እንደ ሚዳቋ ከአዳኝ እጅ፥
እንደ ወፍም ከአጥማጅ እጅ ትድን ዘንድ።
6አንተ ሰነፍ፥ ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፥
መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን።
7አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት
8መብሏን በበጋ ታሰናዳለች፥
መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች።
9አንተ ሰነፍ፥ እስከ መቼ ትተኛለህ?
ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ?
10 #
ምሳ. 24፥33፤34። ጥቂት መተኛት፥ ጥቂት ማንቀላፋት፥
ለመተኛት ጥቂት እጅን ማጣጠፍ፥
11እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥
ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።
12ከንቱና ክፉ ሰው
ጠማማ ንግግር ይዞ ይዞራል፥
13 #
ሲራ. 27፥22። በዓይኑ ይጠቅሳል፥ በእግሩ ይናገራል፥
በጣቱ ያስተምራል፥
14ጠማማነት በልቡ አለ፥ ሁልጊዜም ክፋትን ያቅዳል፥
ጠብንም ይዘራል።
15ስለዚህ ጥፋት ድንገት ይደርስበታል፥
ድንገት ይደቅቃል፥ ፈውስም ከቶ የለውም።
16ጌታ የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥
ሰባተኛውንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፋቸዋለች፥
17ትዕቢተኛ ዐይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥
ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
18ክፉ አሳብን የሚያቅድ ልብ፥
ወደ ክፉ የሚሮጡ እግሮች፥
19በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
20ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥
የእናትህንም ትምህርት አትተው፥
21ሁልጊዜም በልብህ አኑራቸው፥
በአንገትህም እሰራቸው።
22ስትሄድም ይመሩሃል፥
ስትተኛ ይጠብቁሃል፥
ስትነሣ ያነጋግሩሃል።
23ትእዛዝ መብራት፥ ትምህርትም ብርሃን ነውና፥
የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና፥
24ከክፉ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ
ከሌላይቱም ሴት አታላይ ምላስ።
25ውበትዋን በልብህ አትመኘው፥
በዐይኖችዋም አትማረክ።
26የሴተኛ ዐዳሪዋ ዋጋ እስከ አንዲት እንጀራ ነው፥
አመንዝራም ሴት የሰውን ሕይወት ታጠምዳለች።
27በጉያው እሳትን የሚታቀፍ፥
ልብሶቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው?
28በፍም ላይ የሚሄድ
እግሮቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው?
29ወደ ሰው ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፥
የሚነካትም ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም።
30ሌባ በተራበ ጊዜ ነፍሱን ሊያጠግብ ቢሰርቅ
ሰዎች አይንቁትም፥
31ቢያዝም ሰባት እጥፍ ይከፍላል፥
በቤቱም ያለውን ሁሉ ይሰጣል።
32ከሴት ጋር የሚያመነዝር ግን አእምሮ የጐደለው ነው፥
እንዲሁም የሚያደርግ ነፍሱን ያጠፋል።
33ቁስልንና ውርደትን ያገኛል፥
ስድቡም አይደመሰስም።
34ቅንዓት ለሰው የቁጣ ትኩሳት ነውና፥
በበቀልም ቀን አይራራለትምና።
35እርሱም ምንም ካሣ አይቀበልም፥
ስጦታም ብታበዛለት አይታረቅም።