መዝሙረ ዳዊት 113
113
1 #
መዝ. 135፥1። ሃሌ ሉያ።
የጌታ አገልጋዮች ሆይ፥ አመስግኑት፥
የጌታንም ስም አመስግኑ።
2ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ
የጌታ ስም ቡሩክ ይሁን።
3 #
ሚል. 1፥11። ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ
የጌታ ስም ይመስገን።
4 #
መዝ. 148፥13። ጌታ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ልዑል ነው፥
ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።
5እንደ ጌታ እንደ እግዚአብሔር የሚሆን ማን ነው?
በላይ የሚኖር፥
6 #
መዝ. 89፥7-9። በሰማይና በምድር ያሉትን ለማየት ዝቅ የሚል፥
7-8 #
መዝ. 107፥41፤ 1ሳሙ. 2፥7-8። ከመኰንኖች ጋር ከሕዝቡም መኰንኖች ጋር ያኖረው ዘንድ
ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥
ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ፥
9 #
1ሳሙ. 2፥5፤ ኢሳ. 54፥1። መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥
ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት።
ሃሌ ሉያ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 113: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ