መዝሙረ ዳዊት 114
114
1ሃሌ ሉያ! #ዘፀ. 12፥51።እስራኤል ከግብጽ፥
የያዕቆብም ቤት ከእንግዳ ሕዝብ በወጣ ጊዜ፥
2ይሁዳ መቅደሱ፥
እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።
3 #
መዝ. 66፥6፤ 74፥15፤ ዘፀ. 14፥21፤ ኢያ. 3፥14። ባሕር አየች፥ ሸሸችም፥
ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
4 #
መዝ. 29፥6፤ ጥበ. 19፥9። ተራሮች እንደ አውራ በጎች፥
ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ።
5አንቺ ባሕር የሸሸሽው፥
አንቺስ ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽው፥ ምን ሆናችሁ ነው?
6እናንተም ተራሮች፥ እንደ አውራ በጎች፥
ኮረብቶችስ፥ እንደ ጠቦቶች ለምን ዘለላችሁ?
7 #
መዝ. 68፥9። በያዕቆብ አምላክ ፊት፥
በጌታ ፊት ምድር ተናወጠች፥
8 #
ዘፀ. 17፥6፤ ዘኍ. 20፥11። ዐለቱን ወደ ውኃ መቆሚያ፥
ድንጋዩንም ወደ ውኃ ምንጭ ይለውጣል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 114: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ