መዝሙረ ዳዊት 123
123
1የዕርገት መዝሙር።
#
መዝ. 25፥15፤ 119፥82፤ 141፥8። በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዐይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ።
2እነሆ፥ የአገልጋዮች ዐይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥
የአገልጋዪቱም ዐይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደሆነ፥
እንዲሁ እስኪምረን ድረስ
ዓይናችን ወደ ጌታ አምላካችን ነው።
3 #
መዝ. 44፥13-14፤ ኢዮብ 12፥4። ማረን፥ አቤቱ፥ ማረን፥
ብዙ ንቀት አጠግቦናልና፥
4የትምክሕተኞችን ሹፈትና የትዕቢተኞችን ንቀት
ነፍሳችን እጅግ ጠገበች።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 123: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ