መዝሙረ ዳዊት 123

123
1የዕርገት መዝሙር።
# መዝ. 25፥15፤ 119፥82፤ 141፥8። በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዐይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ።
2እነሆ፥ የአገልጋዮች ዐይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥
የአገልጋዪቱም ዐይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደሆነ፥
እንዲሁ እስኪምረን ድረስ
ዓይናችን ወደ ጌታ አምላካችን ነው።
3 # መዝ. 44፥13-14፤ ኢዮብ 12፥4። ማረን፥ አቤቱ፥ ማረን፥
ብዙ ንቀት አጠግቦናልና፥
4የትምክሕተኞችን ሹፈትና የትዕቢተኞችን ንቀት
ነፍሳችን እጅግ ጠገበች።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ