መዝሙረ ዳዊት 125

125
1የዕርገት መዝሙር።
# ምሳ. 10፥25። በጌታ የታመኑ
እንደማይታወክ ለዘለዓለም እንደሚኖር
እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።
2 # ዘዳ. 32፥11። ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ፥
ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም
ጌታ በሕዝቡ ዙሪያ ነው።
3ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ
የክፉዎች በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም።
4 # መዝ. 18፥25። አቤቱ፥ ለመልካሞች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።
5 # መዝ. 128፥6፤ ምሳ. 3፥32። ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን
ዓመፅን ከሚሠሩት ጋር ጌታ ይወስዳቸዋል።
ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ