መዝሙረ ዳዊት 126

126
1የዕርገት መዝሙር።
# መዝ. 14፥7። ጌታ የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥
ሕልም የምናይ መስሎን ነበር።
2 # ኢዮብ 8፥21። በዚያን ጊዜ አፋችን በሳቅ፥
አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፥
በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ፦
ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ።
3ጌታ ለኛ ታላቅ ነገርን አደረገልን፥
ደስም አለን።
4አቤቱ፥ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች
ምርኮአችንን መልስ።
5 # ባሮክ 4፥23፤ ኢሳ. 65፥19። በዕንባ የሚዘሩ በእልልታ ይለቅማሉ።
6መሄድስ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፥
መመለስስ፥ ነዶአቸውን ተሸክመው በእልልታ ይመጣሉ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ