መዝሙረ ዳዊት 128
128
1የመዓርግ መዝሙር።
#
መዝ. 112፥1። ጌታን የሚፈሩት ሁሉ፥
በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።
2 #
መዝ. 112፥3። የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፥
ምስጉን ነህ፤ መልካምም ይሆንልሃል።
3 #
መዝ. 144፥12፤ ኢዮብ 29፥5። ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፥
ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።
4እነሆ፥ ጌታን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።
5 #
መዝ. 20፥3፤ 134፥3። ጌታ ከጽዮን ይባርክህ፥
በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥
የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ።
6 #
ኢዮብ 42፥16፤ መዝ. 125፥5፤ ምሳ. 17፥6። የልጆችህንም ልጆች ታያለህ።
በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 128: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ