መዝሙረ ዳዊት 129

129
1የዕርገት መዝሙር።
# መዝ. 124፥1። እስራኤል፦ “ከትንሽነቴ ጀምሮ አብዝተው አጠቁኝ” ይበል፥
2 # መዝ. 118፥13። ከትንሽነቴ ጀምሮ አብዝተው አጠቁኝ፥
ነገር ግን አላሸነፉኝም።
3 # ኢሳ. 51፥23። አራሾች በጀርባዬ ላይ አረሱ፥
ትልማቸውን አስረዘሙ።#129፥3 ጅርባዬን በጅራፍ ተለተሉ
4ጌታ ጻድቅ ነው፥
የክፉዎችን ገመድ ቈረጠ።
5ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥
ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።
6 # ኢሳ. 37፥27። በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥
ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥
7ለሚያጭደው እጁን፥
ነዶዎቹን ለሚሰበስብ እቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።
8 # መዝ. 118፥26። በመንገድም የሚያልፉ፦ የጌታ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፥
በጌታ ስም እንመርቃችኋለን አይሉም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ