መዝሙረ ዳዊት 130

130
1የዕርገት መዝሙር።
አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ።
2 # መዝ. 5፥2-3፤ 55፥2-3፤ 86፥6፤ ሰቆ.ኤ. 3፥55-56፤ ዮናስ 2፥3። አቤቱ፥ ድምፄን ስማ፥
ጆሮህ የልመናዬን ቃል ያድምጥ።
3 # ናሆም 1፥6። አቤቱ፥ ኃጢአትን ብትይዝ፥
አቤቱ፥ ማን ይቆማል?
4ይቅርታ በአንተ ዘንድ ነውና።
5 # መዝ. 119፥81። አቤቱ ተስፋ አደረግሁ፥
ነፍሴ ጠበቀች፥ በቃሉ ታመንኩ።
6 # ኢሳ. 21፥11፤ 26፥9። ማለዳን ከሚጠብቁ የሌሊት ጠባቂዎች ይልቅ፥
ነፍሴ ጌታን ትጠብቃለች፥ ማለዳን ከሚጠብቁ ጠባቂዎች ይልቅ።
7 # መዝ. 86፥15፤ 100፥5፤ 103፥8። ከጌታ ጋር ጽኑ ፍቅር፥
በእርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን አለና
እስራኤል በጌታ ይታመን።
8 # መዝ. 25፥22፤ ማቴ. 1፥21። እርሱም እስራኤልን ከበደሉ ሁሉ ያድነዋል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ