መዝሙረ ዳዊት 132

132
1የዕርገት መዝሙር።
አቤቱ፥ ዳዊትን፥ መከራውንም ሁሉ አስታውስ፥
2ለጌታ እንደማለ፥
ለያዕቆብም ኀያል#132፥2 አምላክ። እንደ ተሳለ፦
3 # 2ሳሙ. 7፤ 1ዜ.መ. 28፥2። በእውነት ወደ ቤቴ ድንኳን አልገባም፥
ወደ ምንጣፌም አልጋ አልወጣም፥
4ለዐይኖቼም መኝታ፥
ለሽፋሽፍቶቼም እንቅልፍ#132፥4 ሰባ ሊቃናት “ለዐይን ሥቤ” ወይም “ለጉንጮቼም ዕረፍትን” የሚለውን ይጨምራል። አልሰጥም፥
5ለጌታ ስፍራ፥
ለያዕቆብ ኀያል ማደሪያ እስካገኝ ድረስ ብሎ።
6እነሆ፥ በኤፍራታ ሰማነው፥
በጁኦሪም ምድር አገኘነው።
7 # መዝ. 99፥5። ወደ ማደሪያዎቹ እንግባ፥
እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንስገድ።
8 # መዝ. 2፥2፤ 89፥21፤ 95፥11፤ ዘኍ. 10፥35፤ 2ዜ.መ. 6፥41-42፤ ሲራ. 24፥7። አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥
አንተና የመቅደስህ ታቦት።
9ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፥
ጻድቃንህም ደስ ይበላቸው።
10ስለ ዳዊት ስለ ባርያህ ብለኽ
የቀባኸውን ሰው ፊት አትመልስ።
11 # መዝ. 68፥17፤ 1ነገ. 8፥13፤ ሲራ. 24፥7። ጌታ ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትምም፥
እንዲህ ብሎ፦ ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።#መዝ. 110፥4፤ 2ሳሙ. 7፥12።
12ልጆችህ ኪዳኔን፥
ይህንም የማስተማራቸውን ኪዳኔን ቢጠብቁ፥
ልጆቻቸው ደግሞ በዙፋንህ ላይ ለዘለዓለም ይቀመጣሉ።
13ጌታ ጽዮንን መርጦአታልና፥
ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦
14“ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፥
መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።
15ስንቆቿን እጅግ እባርካለሁ፥
ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።
16 # 2ዜ.መ. 6፥41፤ ኢሳ. 61፥10። ካህናትዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥
ጻድቃኗም እጅግ ደስ ይላቸዋል።
17 # ኢሳ. 11፥1፤ ኤር. 33፥15፤ ሕዝ. 29፥21፤ ዘካ. 3፥8፤ ሉቃ. 1፥69። በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ#132፥17 ኃይልን እሰጣለሁ።
ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ።
18ጠላቶቹንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፥
በእርሱ ግን ዘውዱ ያንጸባርቃል።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ