መዝሙረ ዳዊት 16
16
1የዳዊት ቅኔ።
#
መዝ. 25፥20። አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ።
2ጌታን፦ “አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ”፥
ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።
3ደስታዬ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳንና ክቡራን ላይ ነው።
4ወደ ሌላ አምላክ ለሚፋጠኑት መከራቸው ይበዛል፥
የቁርባናቸውን ደም እኔ አላፈስሰውም፥
ስማቸውንም በከንፈሬ አልጠራም።
5 #
መዝ. 23፥5፤ 73፥26፤ ዘኍ. 18፥20፤ ሰቆ.ኤ. 3፥24። ጌታ የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥
ዕጣ ፈንታዬንም የምታጸና አንተ ነህ።
6ገመድ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ፥
ርስቴም ተዋበችልኝ።
7የመከረኝን አምላክ እባርካለሁ፥
ደግሞም በሌሊት ኩላሊቶቼ#16፥7 ኅሊናዬ ይገሥጹኛል።
8 #
መዝ. 73፥23፤ 121፥5፤ 8፤ የሐዋ. 2፥25-28። ሁልጊዜ ጌታን በፊቴ አየዋለሁ፥
በቀኜ ነውና አልታወክም።
9ስለዚህ ልቤን ደስ አለው
ነፍሴም ሐሴት አደረገች፥
ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች፥
10 #
መዝ. 28፥1፤ 30፥4፤ 49፥16፤ 86፥13፤ ዮናስ 2፥7፤ የሐዋ. 13፥35። ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥
ቅዱስህንም መበስበስን#16፥10 ጉድጓድ ያይ ዘንድ ያይ ዘንድ አትተወውም።
11 #
የሐዋ. 2፥25-28። የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፥
ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥
በቀኝህም የዘለዓለም ፍሥሐ አለ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 16: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ