የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 2

2
1 # የሐዋ. 4፥25፤26፤ ራእ. 11፥18። አሕዛብ ለምን ያጉረመርማሉ?
ለምንስ ከንቱዉን ያሰላስላሉ?
2 # መዝ. 83፥6። የምድር ነገሥታት ተነሡ፥
አለቆችም በጌታና በመሢሑ ላይ ተማከሩ፦
3 # መዝ. 149፥8። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥
ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል#2፥3 ማሰርያውና ገመዱ የእግዚእብሔርና የንጉሡ ወይም የመሢሑ ነው።
4 # መዝ. 37፥13፤ 59፥9፤ ጥበ. 4፥18። በሰማያት የሚቀመጠውም እርሱ ይሥቃል፥
ጌታም ይሣለቅባቸዋል።
5በዚያን ጊዜ በቁጣው ይናገራቸዋል፥
በመዓቱም ያውካቸዋል።
6እኔ ግን ንጉሤን#2፥6 እግዚአብሔር የሾመው ንጉሥ ማለት ነው። ሾምሁ
በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።
7 # መዝ. 89፥27፤ 110፥2-3፤ ኢሳ. 49፥1፤ የሐዋ. 13፥33፤ ዕብ. 1፥5፤ 5፥5። ትእዛዙን እናገራለሁ፥#2፥7 እዚህ ላይ የሚናገረው ንጉሡ ነው።
ጌታ አለኝ፦ “አንተ ልጄ ነህ፥
እኔ ዛሬ ወለድሁህ።”
8ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ
የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።
9 # ራእ. 2፥26-27፤ 12፥5፤ 19፥15። በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ፥
እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ታደቃቸዋለህ።
10አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፥
እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ።
11 # መዝ. 34፥9፤ 146፥5፤ ምሳ. 16፥20። ለጌታ በፍርሃት ተገዙ፥
በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
12ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ
እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥
ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና።
በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ