መዝሙረ ዳዊት 3
3
1ከልጁ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸ ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
2አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ!
በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።
3 #
መዝ. 71፥11። ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦
አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።
4 #
መዝ. 7፥11፤ 18፥3፤ 62፥7-8፤ ዘዳ. 33፥29፤ ኢሳ. 60፥19። አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ጋሻዬ ነህ፥
ክብሬና ራሴንም ቀና የምታደርገው አንተ ነህ።
5በሙሉ ድምጽ ወደ ጌታ እጮሃለሁ፥
ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።
6 #
መዝ. 4፥9፤ ምሳ. 3፥24። እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፥
ጌታም ደግፎኛልና ነቃሁ።
7የሚከቡኝን አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
8 #
መዝ. 58፥7። ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፥
አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥
የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።
9 #
መዝ. 28፥9፤ ዮናስ 2፥10። ማዳን የጌታ ነው፥
በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 3: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 3
3
1ከልጁ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸ ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
2አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ!
በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።
3 #
መዝ. 71፥11። ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦
አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።
4 #
መዝ. 7፥11፤ 18፥3፤ 62፥7-8፤ ዘዳ. 33፥29፤ ኢሳ. 60፥19። አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ጋሻዬ ነህ፥
ክብሬና ራሴንም ቀና የምታደርገው አንተ ነህ።
5በሙሉ ድምጽ ወደ ጌታ እጮሃለሁ፥
ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።
6 #
መዝ. 4፥9፤ ምሳ. 3፥24። እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፥
ጌታም ደግፎኛልና ነቃሁ።
7የሚከቡኝን አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
8 #
መዝ. 58፥7። ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፥
አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥
የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።
9 #
መዝ. 28፥9፤ ዮናስ 2፥10። ማዳን የጌታ ነው፥
በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።