መዝሙረ ዳዊት 20
20
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2በመከራ ቀን ጌታ ይስማህ፥
የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምህ።
3 #
መዝ. 128፥5፤ 134፥3። ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥
ከጽዮንም ይደግፍህ።
4መባዎችህን ሁሉ ያስብልህ፥
የሚቃጠል መሥዋዕትህን ያለምልምልህ።
5እንደ ልብህ ምኞት ይስጥህ
ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።
6በማዳንህ ደስ ይለናል፥
በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፥
ልመናህን ሁሉ ጌታ ይፈጽምልህ።
7 #
መዝ. 18፥51፤ 144፥10፤ 1ሳሙ. 2፥10። ጌታ የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ አወቅሁ፥
ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል፥
በቀኙ ብርታት ማዳን አለና።
8 #
መዝ. 147፥10-11፤ 2ዜ.መ. 14፥10፤ ምሳ. 21፥31፤ 1ሳሙ. 17፥45፤ ኢሳ. 31፥1፤ 36፥9። እነኚህ በሠረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፥
እኛ ግን በአምላካችን በጌታ ስም ከፍ ከፍ እንላለን።
9 #
ኢሳ. 40፥30። እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፥
እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን።
10አቤቱ፥ ንጉሥን አድነው፥
በጠራንህም ቀን ስማን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 20: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ