መዝሙረ ዳዊት 24
24
1የዳዊት መዝሙር#24፥1 የግሪኩ ንባብ “በመጀመሪያ ሰንበት” የሚል ቃል ይጭምራል። ።
#
መዝ. 50፥12፤ 89፥12፤ ዘዳ. 10፥14፤ 1ቆሮ. 10፥26። ምድርና ሞላዋ የጌታ ናቸው፥
ዓለምና በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ።
2 #
መዝ. 136፥6፤ ኢሳ. 42፥5። እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቶአታልና፥
በፈሳሾችም ላይ አጽንቶአታልና።
3 #
መዝ. 15፥1። ወደ ጌታ ተራራ ማን ይወጣል?
በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል?
4 #
ማቴ. 5፥8። እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥
ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥
በሽንገላ ያልማለ።
5እርሱ ከጌታ ዘንድ በረከትን
ከመድኃኒቱ አምላክም ጽድቅን ይቀበላል።
6ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥
የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ።
7 #
መዝ. 118፥19-20። እናንት በሮች#24፥7 የግሪኩ ትርጒም “እናንት መኳንንቶች በሮችን ክፈቱ” ይላል። የዕብራይስጡ ንባብ ግን በሮች ቀና እንዲሉ ወይም ራሳቸውን ከፍ እንዲያደርጉ ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ይገልጻል። አባባሉ ምሳሌአዊ ነው። ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፥
የዘለዓለም ደጆችም ተከፈቱ፥
የክብርም ንጉሥ ይግባ።
8ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
ጌታ ነው፥ ብርቱና ኃያል፥
ጌታ ነው፥ በሰልፍ ኃያል።
9እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፥
የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ፥
የክብርም ንጉሥ ይግባ።
10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
የሠራዊት ጌታ
እርሱ የክብር ንጉሥ ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 24: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ