መዝሙረ ዳዊት 25
25
1የዳዊት መዝሙር።
አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
2 #
መዝ. 71፥1፤ መዝ. 86፥4፤ 143፥8። አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ አልፈር፥
ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
3 #
መዝ. 22፥6፤ ኢሳ. 49፥23፤ ዳን. 3፥40። አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፥
በከንቱ የሚከዱ ያፍራሉ።
4 #
መዝ. 27፥11፤ 86፥11፤ 119፥12፤ 35፤ 143፥8፤ 10። አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥
ፈለግህንም አስተምረኝ።
5አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና
በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም፥
ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
6 #
ሲራ. 51፥8። አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥
ከጥንት ጀምሮ ናቸውና።
7 #
ኢዮብ 13፥26፤ ኢሳ. 64፥8። የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ፥
አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ።
8ጌታ ቸርና ቅን ነው፥
ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።
9ትሑታንን በፍርድ ይመራል፥
ለትሑታን መንገድን ያስተምራቸዋል።
10የጌታ መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው
ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ።
11አቤቱ፥ በደሌ ብዙ ነውና
ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።
12 #
ምሳ. 19፥23። ጌታን የሚፈራ ሰው ማን ነው?
በሚመርጠው መንገድ እርሱን ያስተምረዋል።
13 #
መዝ. 37፥9፤ 29። ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥
ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
14ጌታ ለሚፈሩት ወዳጃቸው ነው፥
ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።
15 #
መዝ. 123፥1፤ 2፤ 141፥8። እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና
ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ ጌታ ናቸው።
16 #
መዝ. 86፥16፤ 119፥132። እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ ነኝና
ፊትህን ወደ እኔ መልስ ማረኝም።
17የልቤ ችግር ብዙ ነው፥
ከጭንቀቴ አውጣኝ።
18ድካሜንና መከራዬን እይ፥
ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
19ጠላቶቼ እንደበዙ እይ፥
የግፍም ጥል ጠልተውኛል።
20ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ፥
አንተን ታምኛለሁና አልፈር።
21አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና
ፍጽምናና ቅንነት ይጠብቁኝ።
22አቤቱ፥ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 25: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 25
25
1የዳዊት መዝሙር።
አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
2 #
መዝ. 71፥1፤ መዝ. 86፥4፤ 143፥8። አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ አልፈር፥
ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
3 #
መዝ. 22፥6፤ ኢሳ. 49፥23፤ ዳን. 3፥40። አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፥
በከንቱ የሚከዱ ያፍራሉ።
4 #
መዝ. 27፥11፤ 86፥11፤ 119፥12፤ 35፤ 143፥8፤ 10። አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥
ፈለግህንም አስተምረኝ።
5አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና
በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም፥
ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
6 #
ሲራ. 51፥8። አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥
ከጥንት ጀምሮ ናቸውና።
7 #
ኢዮብ 13፥26፤ ኢሳ. 64፥8። የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ፥
አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ።
8ጌታ ቸርና ቅን ነው፥
ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።
9ትሑታንን በፍርድ ይመራል፥
ለትሑታን መንገድን ያስተምራቸዋል።
10የጌታ መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው
ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ።
11አቤቱ፥ በደሌ ብዙ ነውና
ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።
12 #
ምሳ. 19፥23። ጌታን የሚፈራ ሰው ማን ነው?
በሚመርጠው መንገድ እርሱን ያስተምረዋል።
13 #
መዝ. 37፥9፤ 29። ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥
ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
14ጌታ ለሚፈሩት ወዳጃቸው ነው፥
ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።
15 #
መዝ. 123፥1፤ 2፤ 141፥8። እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና
ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ ጌታ ናቸው።
16 #
መዝ. 86፥16፤ 119፥132። እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ ነኝና
ፊትህን ወደ እኔ መልስ ማረኝም።
17የልቤ ችግር ብዙ ነው፥
ከጭንቀቴ አውጣኝ።
18ድካሜንና መከራዬን እይ፥
ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
19ጠላቶቼ እንደበዙ እይ፥
የግፍም ጥል ጠልተውኛል።
20ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ፥
አንተን ታምኛለሁና አልፈር።
21አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና
ፍጽምናና ቅንነት ይጠብቁኝ።
22አቤቱ፥ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።