መዝሙረ ዳዊት 26
26
1የዳዊት መዝሙር።
#
መዝ. 7፥9። አቤቱ፥ እኔ በቅንነት ሄጃለሁና ፍረድልኝ፥
በጌታም አምኛለሁና አልናወጥም።
2 #
መዝ. 17፥3፤ 139፥23። አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፥
ኩላሊቴንና ልቤን መርምር።
3 #
መዝ. 86፥11። ቸርነትህ በዓይኔ ፊት ነውና፥
በእውነትህም ተመላለስሁ።
4ከአታላዮች ጋር አልተቀመጥሁም፥
ከአስመሳዮችም ጋር አልገባሁም።
5የክፉ አድራጊዎቸን ማኅበር ጠላሁ፥
ከክፉዎችም ጋር አልቀመጥም።
6 #
መዝ. 73፥13። እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፥
አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥
7የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፥
ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
8 #
መዝ. 29፥9፤ 63፥3፤ ዘፀ. 24፥16፤ 25፥8። አቤቱ፥ የቤትህን ስፍራ
የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።
9 #
መዝ. 28፥3። ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥
ከደም ሰዎችም#26፥9 ነፍሰ ገዳዮች ጋር ሕይወቴን አታጥፋ።
10በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥
ቀኛቸውም በጉቦ ተሞልታለች።
11 #
መዝ. 101፥6፤ መዝ. 25፥16። እኔ ግን በቅንነት ሄጃለሁ፥
አድነኝ ማረኝም።
12 #
መዝ. 22፥23፤ 35፥18፤ 149፥1። እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፥
አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 26: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 26
26
1የዳዊት መዝሙር።
#
መዝ. 7፥9። አቤቱ፥ እኔ በቅንነት ሄጃለሁና ፍረድልኝ፥
በጌታም አምኛለሁና አልናወጥም።
2 #
መዝ. 17፥3፤ 139፥23። አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፥
ኩላሊቴንና ልቤን መርምር።
3 #
መዝ. 86፥11። ቸርነትህ በዓይኔ ፊት ነውና፥
በእውነትህም ተመላለስሁ።
4ከአታላዮች ጋር አልተቀመጥሁም፥
ከአስመሳዮችም ጋር አልገባሁም።
5የክፉ አድራጊዎቸን ማኅበር ጠላሁ፥
ከክፉዎችም ጋር አልቀመጥም።
6 #
መዝ. 73፥13። እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፥
አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥
7የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፥
ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
8 #
መዝ. 29፥9፤ 63፥3፤ ዘፀ. 24፥16፤ 25፥8። አቤቱ፥ የቤትህን ስፍራ
የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።
9 #
መዝ. 28፥3። ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥
ከደም ሰዎችም#26፥9 ነፍሰ ገዳዮች ጋር ሕይወቴን አታጥፋ።
10በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥
ቀኛቸውም በጉቦ ተሞልታለች።
11 #
መዝ. 101፥6፤ መዝ. 25፥16። እኔ ግን በቅንነት ሄጃለሁ፥
አድነኝ ማረኝም።
12 #
መዝ. 22፥23፤ 35፥18፤ 149፥1። እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፥
አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።