መዝሙረ ዳዊት 29
29
1ከድንኳን በሚወጣበት ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።
የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለጌታ አምጡ።
ክብርንና ምስጋናን ለጌታ አምጡ።
2 #
መዝ. 68፥35፤ 96፥7-9። የስሙን ክብር ለጌታ አምጡ፥
በቅድስናው ስፍራ ለጌታ ስገዱ።
3የጌታ ድምፅ በውኆች ላይ፥
የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥
አምላክ በብዙ ውኆች ላይ።
4 #
መዝ. 46፥7፤ 77፥18-19፤ ኢዮብ 37፥4፤ ኢሳ. 30፥30። የጌታ ድምፅ በኃይል ነው፥
የጌታ ድምፅ በታላቅ ክብር የተሞላ ነው።
5የጌታ ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፥
ጌታ የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
6እንደ ጥጃ ሊባኖስን#29፥6 የሊባኖስን ተራራዎች፥
እንደ ጎሽ ጥጃ ስርዮንን#29፥6 የሔርሞን ተራራ ያዘልላቸዋል።
7የጌታ ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
8የጌታ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፥
ጌታ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9የጌታ ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥
ጫካዎቹንም ይገልጣል፥
ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
10 #
ባሮክ 3፥3። ጌታ የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፥
ጌታ ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
11 #
መዝ. 68፥36። ጌታ ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፥
ጌታ ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 29: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 29
29
1ከድንኳን በሚወጣበት ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።
የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለጌታ አምጡ።
ክብርንና ምስጋናን ለጌታ አምጡ።
2 #
መዝ. 68፥35፤ 96፥7-9። የስሙን ክብር ለጌታ አምጡ፥
በቅድስናው ስፍራ ለጌታ ስገዱ።
3የጌታ ድምፅ በውኆች ላይ፥
የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥
አምላክ በብዙ ውኆች ላይ።
4 #
መዝ. 46፥7፤ 77፥18-19፤ ኢዮብ 37፥4፤ ኢሳ. 30፥30። የጌታ ድምፅ በኃይል ነው፥
የጌታ ድምፅ በታላቅ ክብር የተሞላ ነው።
5የጌታ ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፥
ጌታ የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
6እንደ ጥጃ ሊባኖስን#29፥6 የሊባኖስን ተራራዎች፥
እንደ ጎሽ ጥጃ ስርዮንን#29፥6 የሔርሞን ተራራ ያዘልላቸዋል።
7የጌታ ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
8የጌታ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፥
ጌታ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9የጌታ ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥
ጫካዎቹንም ይገልጣል፥
ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
10 #
ባሮክ 3፥3። ጌታ የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፥
ጌታ ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
11 #
መዝ. 68፥36። ጌታ ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፥
ጌታ ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።