መዝሙረ ዳዊት 30
30
1ለቤቱ መመረቅ ምስጋና፥ የዳዊት መዝሙር።
2አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥
ጠላቶቼንም ደስ አላሰኘህብኝምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።
3አቤቱ አምላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ አንተም ፈወስከኝ።
4 #
መዝ. 28፥1፤ ዮናስ 2፥7። አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥
ወደ ጉድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።
5ቅዱሳን ሆይ፥ ለጌታ ዘምሩ፥
ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።
6ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፥
ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን፥
ልቅሶ ማታ ይመጣል፥
ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።
7እኔም በደስታዬ፦ ለዘለዓለም አልታወክም አልሁ።
8 #
መዝ. 104፥29። አቤቱ፥ በፈቃድህ እንደ ጽኑ ተራራ አጠነከርከኝ፥
ፊትህን ስትሰውር፥ እኔም ደነገጥሁ።
9አቤቱ፥ ወደ አንተ ጠራሁ፥
ወደ አምላኬም ለመንሁ።
10ወደ ጉድጓድ ብወርድ ከደሜ ምን ጥቅም ይገኛል?
አፈር ያመሰግንሃልን? እውነትህንም ይናገራልን?
11ጌታ ሰማ ማረኝም፥
ጌታ ረዳቴ ሆነኝ።
12 #
ኢሳ. 61፥3፤ ኤር. 31፥13። ልቅሶዬን ወደ እልልታ ለወጥህልኝ፥
ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ።
13ክብሬ ትዘምርልህ ዘንድ ዝምም እንዳትል፥
አቤቱ አምላኬ፥ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 30: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 30
30
1ለቤቱ መመረቅ ምስጋና፥ የዳዊት መዝሙር።
2አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥
ጠላቶቼንም ደስ አላሰኘህብኝምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።
3አቤቱ አምላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ አንተም ፈወስከኝ።
4 #
መዝ. 28፥1፤ ዮናስ 2፥7። አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥
ወደ ጉድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።
5ቅዱሳን ሆይ፥ ለጌታ ዘምሩ፥
ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።
6ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፥
ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን፥
ልቅሶ ማታ ይመጣል፥
ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።
7እኔም በደስታዬ፦ ለዘለዓለም አልታወክም አልሁ።
8 #
መዝ. 104፥29። አቤቱ፥ በፈቃድህ እንደ ጽኑ ተራራ አጠነከርከኝ፥
ፊትህን ስትሰውር፥ እኔም ደነገጥሁ።
9አቤቱ፥ ወደ አንተ ጠራሁ፥
ወደ አምላኬም ለመንሁ።
10ወደ ጉድጓድ ብወርድ ከደሜ ምን ጥቅም ይገኛል?
አፈር ያመሰግንሃልን? እውነትህንም ይናገራልን?
11ጌታ ሰማ ማረኝም፥
ጌታ ረዳቴ ሆነኝ።
12 #
ኢሳ. 61፥3፤ ኤር. 31፥13። ልቅሶዬን ወደ እልልታ ለወጥህልኝ፥
ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ።
13ክብሬ ትዘምርልህ ዘንድ ዝምም እንዳትል፥
አቤቱ አምላኬ፥ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።