የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 37

37
1የዳዊት መዝሙር።
# ምሳ. 3፥31፤ 23፥17፤ 24፥1፤ 19። በክፉዎች ላይ አትቅና፥
ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፥
2 # መዝ. 90፥5-6፤ 102፥12፤ 103፥15-16፤ ኢዮብ 14፥2፤ ኢሳ. 40፥7። እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥
እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና።
3 # መዝ. 128፥1-2። በጌታ ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥
በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።
4 # ምሳ. 10፥24። በጌታ ደስ ይበልህ፥
የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
5 # መዝ. 55፥23፤ ምሳ. 3፥5፤ 16፥3። መንገድህን ለጌታ አደራ ስጥ፥
በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።
6 # ጥበ. 5፥6፤ ኢሳ. 58፥10። ጽድቅህን እንደ ብርሃን።
ፍርድህንም እንደ ቀትር ያመጣዋል።
7በጌታ ጽና በተዕግሥትም ጠብቀው።
መንገዱም በቀናችለትና በሚያደባ ሰው አትቅና።
8ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው፥
እንዳትበድል አትቅና።
9 # መዝ. 25፥13፤ ምሳ. 2፥21፤ ኢሳ. 57፥13። ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፥
በጌታ ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ።
10ጥቂት ጊዜ ቆይቶ፥ ክፉ አድራጊ አይኖርም፥
ትፈልገዋለህ ቦታውንም አታገኝም።
11 # ማቴ. 5፥5። ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፥
በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።
12ክፉ በጻድቁ ላይ ያደባል፥
ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያንገጫግጫል።
13 # መዝ. 2፥4፤ 59፥9፤ ጥበ. 4፥18። ጌታ ግን ይሥቅበታል፥
ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና።
14 # መዝ. 11፥2፤ 57፥5፤ 64፥4። ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፥
ቀስታቸውንም ገተሩ
ድሀውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ፥
ልበ ቅኖችንም ይወጉ ዘንድ፥
15ሰይፋቸው ወደ ልባቸው ይግባ፥
ቀስታቸውም ይሰበር።
16 # ምሳ. 15፥16፤ 16፥8። በጻድቅ ዘንድ ያለው ጥቂት ነገር
ከብዙ ክፉዎች ሀብት ይበልጣል።
17የክፉዎች ንድ ትሰበራለችና፥
ጌታ ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል።
18የንጹሓንን ቀኖች ጌታ ያውቃል፥
ርስታቸውም ለዘለዓለም ትሆናለች፥
19በክፉ ዘመንም አያፍሩም፥
በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።
20 # ጥበ. 5፥14። ክፉዎቸ ግን ይጠፋሉ፥
የጌታ ጠላቶች እንደ መስክ ውበት፥
እንደ ጢስም ተንነው ይጠፋሉ።
21ክፉ ይበደራል አይከፍልምም፥
ጻድቅ ግን ይራራል ይሰጣልም።
22እርሱን የሚባርኩት ምድርን ይወርሳሉና፥
የሚረግሙት ግን ይጠፋሉ።
23 # ምሳ. 20፥24። መንገዱን በወደደ ጊዜ፥
የሰው አካሄድ በጌታ ይጸናል።
24ቢወድቅም አይጣልም፥
ጌታ እጁን ይዞ ይደግፈዋልና።
25 # ኢዮብ 4፥7፤ ሲራ. 2፥10። ጐለመስሁ አረጀሁም፥
ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።
26ሁልጊዜ ይራራል ያበድርማል፥
ዘሩም በበረከት ይኖራል።
27 # መዝ. 34፥14-16፤ አሞጽ 5፥14። ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፥
ለዘለዓለምም ትኖራለህ።
28ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል
ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥
የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።
29 # መዝ. 25፥13፤ ምሳ. 2፥21፤ ኢሳ. 57፥13። ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፥
በእርሷም ለዘለዓለም ይኖራሉ።
30 # ምሳ. 10፥31። የጻድቅ አፍ ጥበብን ያናገራል፥
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል።
31 # መዝ. 40፥9፤ ዘዳ. 6፥6፤ ኢሳ. 51፥7፤ ኤር. 31፥33። የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥
በእርምጃውም አይሰናከልም።
32ክፉ ጻድቁን ይመለከተዋል፥
ሊገድለውም ይወድዳል።
33ጌታ ግን በእጁ አይተወውም፥
በፍርድም እንዲሸነፍ አይፈቅድም።
34 # መዝ. 31፥24። በጌታ ተስፋ አድርግ፥ መንገዱንም ጠብቅ፥
ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፥
ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ።
35 # መዝ. 92፥8-9፤ ኢሳ. 2፥13፤ ሕዝ. 31፥10-11። ክፉን በጭቆና ከፍ ከፍ ብሎ
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት።
36ብመለስ ግን አጣሁት፥
ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም።
37 # ምሳ. 23፥18፤ 24፥14። ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም እይ፥
ለሰላም ሰው ተተኪ ይወጣለታልና።
38በደለኞች በአንድነት ይጠፋሉ፥
የክፉዎቸ ዘር ይጠፋል።
39 # መዝ. 9፥10፤ ኢሳ. 25፥4። የጻድቃን መድኃኒታቸው በጌታ ዘንድ ነው፥
በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው።
40ጌታ ይረዳቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥
ከከፉዎችም እጅ ያወጣቸዋል፥
ያድናቸዋልም፥ በእርሱ ታምነዋልና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ