መዝሙረ ዳዊት 37
37
1የዳዊት መዝሙር።
#
ምሳ. 3፥31፤ 23፥17፤ 24፥1፤ 19። በክፉዎች ላይ አትቅና፥
ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፥
2 #
መዝ. 90፥5-6፤ 102፥12፤ 103፥15-16፤ ኢዮብ 14፥2፤ ኢሳ. 40፥7። እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥
እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና።
3 #
መዝ. 128፥1-2። በጌታ ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥
በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።
4 #
ምሳ. 10፥24። በጌታ ደስ ይበልህ፥
የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
5 #
መዝ. 55፥23፤ ምሳ. 3፥5፤ 16፥3። መንገድህን ለጌታ አደራ ስጥ፥
በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።
6 #
ጥበ. 5፥6፤ ኢሳ. 58፥10። ጽድቅህን እንደ ብርሃን።
ፍርድህንም እንደ ቀትር ያመጣዋል።
7በጌታ ጽና በተዕግሥትም ጠብቀው።
መንገዱም በቀናችለትና በሚያደባ ሰው አትቅና።
8ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው፥
እንዳትበድል አትቅና።
9 #
መዝ. 25፥13፤ ምሳ. 2፥21፤ ኢሳ. 57፥13። ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፥
በጌታ ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ።
10ጥቂት ጊዜ ቆይቶ፥ ክፉ አድራጊ አይኖርም፥
ትፈልገዋለህ ቦታውንም አታገኝም።
11 #
ማቴ. 5፥5። ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፥
በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።
12ክፉ በጻድቁ ላይ ያደባል፥
ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያንገጫግጫል።
13 #
መዝ. 2፥4፤ 59፥9፤ ጥበ. 4፥18። ጌታ ግን ይሥቅበታል፥
ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና።
14 #
መዝ. 11፥2፤ 57፥5፤ 64፥4። ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፥
ቀስታቸውንም ገተሩ
ድሀውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ፥
ልበ ቅኖችንም ይወጉ ዘንድ፥
15ሰይፋቸው ወደ ልባቸው ይግባ፥
ቀስታቸውም ይሰበር።
16 #
ምሳ. 15፥16፤ 16፥8። በጻድቅ ዘንድ ያለው ጥቂት ነገር
ከብዙ ክፉዎች ሀብት ይበልጣል።
17የክፉዎች ንድ ትሰበራለችና፥
ጌታ ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል።
18የንጹሓንን ቀኖች ጌታ ያውቃል፥
ርስታቸውም ለዘለዓለም ትሆናለች፥
19በክፉ ዘመንም አያፍሩም፥
በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።
20 #
ጥበ. 5፥14። ክፉዎቸ ግን ይጠፋሉ፥
የጌታ ጠላቶች እንደ መስክ ውበት፥
እንደ ጢስም ተንነው ይጠፋሉ።
21ክፉ ይበደራል አይከፍልምም፥
ጻድቅ ግን ይራራል ይሰጣልም።
22እርሱን የሚባርኩት ምድርን ይወርሳሉና፥
የሚረግሙት ግን ይጠፋሉ።
23 #
ምሳ. 20፥24። መንገዱን በወደደ ጊዜ፥
የሰው አካሄድ በጌታ ይጸናል።
24ቢወድቅም አይጣልም፥
ጌታ እጁን ይዞ ይደግፈዋልና።
25 #
ኢዮብ 4፥7፤ ሲራ. 2፥10። ጐለመስሁ አረጀሁም፥
ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።
26ሁልጊዜ ይራራል ያበድርማል፥
ዘሩም በበረከት ይኖራል።
27 #
መዝ. 34፥14-16፤ አሞጽ 5፥14። ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፥
ለዘለዓለምም ትኖራለህ።
28ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል
ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥
የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።
29 #
መዝ. 25፥13፤ ምሳ. 2፥21፤ ኢሳ. 57፥13። ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፥
በእርሷም ለዘለዓለም ይኖራሉ።
30 #
ምሳ. 10፥31። የጻድቅ አፍ ጥበብን ያናገራል፥
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል።
31 #
መዝ. 40፥9፤ ዘዳ. 6፥6፤ ኢሳ. 51፥7፤ ኤር. 31፥33። የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥
በእርምጃውም አይሰናከልም።
32ክፉ ጻድቁን ይመለከተዋል፥
ሊገድለውም ይወድዳል።
33ጌታ ግን በእጁ አይተወውም፥
በፍርድም እንዲሸነፍ አይፈቅድም።
34 #
መዝ. 31፥24። በጌታ ተስፋ አድርግ፥ መንገዱንም ጠብቅ፥
ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፥
ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ።
35 #
መዝ. 92፥8-9፤ ኢሳ. 2፥13፤ ሕዝ. 31፥10-11። ክፉን በጭቆና ከፍ ከፍ ብሎ
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት።
36ብመለስ ግን አጣሁት፥
ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም።
37 #
ምሳ. 23፥18፤ 24፥14። ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም እይ፥
ለሰላም ሰው ተተኪ ይወጣለታልና።
38በደለኞች በአንድነት ይጠፋሉ፥
የክፉዎቸ ዘር ይጠፋል።
39 #
መዝ. 9፥10፤ ኢሳ. 25፥4። የጻድቃን መድኃኒታቸው በጌታ ዘንድ ነው፥
በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው።
40ጌታ ይረዳቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥
ከከፉዎችም እጅ ያወጣቸዋል፥
ያድናቸዋልም፥ በእርሱ ታምነዋልና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 37: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 37
37
1የዳዊት መዝሙር።
#
ምሳ. 3፥31፤ 23፥17፤ 24፥1፤ 19። በክፉዎች ላይ አትቅና፥
ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፥
2 #
መዝ. 90፥5-6፤ 102፥12፤ 103፥15-16፤ ኢዮብ 14፥2፤ ኢሳ. 40፥7። እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥
እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና።
3 #
መዝ. 128፥1-2። በጌታ ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥
በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።
4 #
ምሳ. 10፥24። በጌታ ደስ ይበልህ፥
የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
5 #
መዝ. 55፥23፤ ምሳ. 3፥5፤ 16፥3። መንገድህን ለጌታ አደራ ስጥ፥
በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።
6 #
ጥበ. 5፥6፤ ኢሳ. 58፥10። ጽድቅህን እንደ ብርሃን።
ፍርድህንም እንደ ቀትር ያመጣዋል።
7በጌታ ጽና በተዕግሥትም ጠብቀው።
መንገዱም በቀናችለትና በሚያደባ ሰው አትቅና።
8ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው፥
እንዳትበድል አትቅና።
9 #
መዝ. 25፥13፤ ምሳ. 2፥21፤ ኢሳ. 57፥13። ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፥
በጌታ ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ።
10ጥቂት ጊዜ ቆይቶ፥ ክፉ አድራጊ አይኖርም፥
ትፈልገዋለህ ቦታውንም አታገኝም።
11 #
ማቴ. 5፥5። ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፥
በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።
12ክፉ በጻድቁ ላይ ያደባል፥
ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያንገጫግጫል።
13 #
መዝ. 2፥4፤ 59፥9፤ ጥበ. 4፥18። ጌታ ግን ይሥቅበታል፥
ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና።
14 #
መዝ. 11፥2፤ 57፥5፤ 64፥4። ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፥
ቀስታቸውንም ገተሩ
ድሀውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ፥
ልበ ቅኖችንም ይወጉ ዘንድ፥
15ሰይፋቸው ወደ ልባቸው ይግባ፥
ቀስታቸውም ይሰበር።
16 #
ምሳ. 15፥16፤ 16፥8። በጻድቅ ዘንድ ያለው ጥቂት ነገር
ከብዙ ክፉዎች ሀብት ይበልጣል።
17የክፉዎች ንድ ትሰበራለችና፥
ጌታ ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል።
18የንጹሓንን ቀኖች ጌታ ያውቃል፥
ርስታቸውም ለዘለዓለም ትሆናለች፥
19በክፉ ዘመንም አያፍሩም፥
በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።
20 #
ጥበ. 5፥14። ክፉዎቸ ግን ይጠፋሉ፥
የጌታ ጠላቶች እንደ መስክ ውበት፥
እንደ ጢስም ተንነው ይጠፋሉ።
21ክፉ ይበደራል አይከፍልምም፥
ጻድቅ ግን ይራራል ይሰጣልም።
22እርሱን የሚባርኩት ምድርን ይወርሳሉና፥
የሚረግሙት ግን ይጠፋሉ።
23 #
ምሳ. 20፥24። መንገዱን በወደደ ጊዜ፥
የሰው አካሄድ በጌታ ይጸናል።
24ቢወድቅም አይጣልም፥
ጌታ እጁን ይዞ ይደግፈዋልና።
25 #
ኢዮብ 4፥7፤ ሲራ. 2፥10። ጐለመስሁ አረጀሁም፥
ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።
26ሁልጊዜ ይራራል ያበድርማል፥
ዘሩም በበረከት ይኖራል።
27 #
መዝ. 34፥14-16፤ አሞጽ 5፥14። ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፥
ለዘለዓለምም ትኖራለህ።
28ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል
ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥
የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።
29 #
መዝ. 25፥13፤ ምሳ. 2፥21፤ ኢሳ. 57፥13። ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፥
በእርሷም ለዘለዓለም ይኖራሉ።
30 #
ምሳ. 10፥31። የጻድቅ አፍ ጥበብን ያናገራል፥
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል።
31 #
መዝ. 40፥9፤ ዘዳ. 6፥6፤ ኢሳ. 51፥7፤ ኤር. 31፥33። የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥
በእርምጃውም አይሰናከልም።
32ክፉ ጻድቁን ይመለከተዋል፥
ሊገድለውም ይወድዳል።
33ጌታ ግን በእጁ አይተወውም፥
በፍርድም እንዲሸነፍ አይፈቅድም።
34 #
መዝ. 31፥24። በጌታ ተስፋ አድርግ፥ መንገዱንም ጠብቅ፥
ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፥
ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ።
35 #
መዝ. 92፥8-9፤ ኢሳ. 2፥13፤ ሕዝ. 31፥10-11። ክፉን በጭቆና ከፍ ከፍ ብሎ
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት።
36ብመለስ ግን አጣሁት፥
ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም።
37 #
ምሳ. 23፥18፤ 24፥14። ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም እይ፥
ለሰላም ሰው ተተኪ ይወጣለታልና።
38በደለኞች በአንድነት ይጠፋሉ፥
የክፉዎቸ ዘር ይጠፋል።
39 #
መዝ. 9፥10፤ ኢሳ. 25፥4። የጻድቃን መድኃኒታቸው በጌታ ዘንድ ነው፥
በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው።
40ጌታ ይረዳቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥
ከከፉዎችም እጅ ያወጣቸዋል፥
ያድናቸዋልም፥ በእርሱ ታምነዋልና።