የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 5

5
1ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 86፥6፤ 130፥1-2። አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥
መቃተቴንም አስተውል፥
3የጩኸቴን ድምፅ አድምጥ፥
ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥
አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።
4 # ጥበ. 16፥28። በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥
በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም።
5አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፥
ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም።
6በከንቱ የሚመኩ በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፥
ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።
7 # መዝ. 101፥7፤ ጥበ. 14፥9፤ ዕብ. 1፥13። ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፥
ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው ጌታ ይጸየፋል።
8 # መዝ. 138፥2፤ ዮናስ 2፥5። እኔ ግን በቸርነትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፥
አንተን በመፍራት ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ።
9 # መዝ. 23፥3፤ ምሳ. 4፥11፤ ኢሳ. 26፥7። አቤቱ፥ በጠላቶቼ ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ፥
መንገዴን በፊትህ አቅና።
10 # ሮሜ 3፥13። በአፋቸው እውነት የለምና፥
ልባቸውም ከንቱ ነው፥
ጉሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥
በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
11 # መዝ. 141፥10። አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፥
ስለ ክፋታቸውም ብዛት አስወግዳቸው፥
እነርሱ ዐምፀውብሃልና።
12 # መዝ. 64፥11። በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ሐሴትን ያድርጉ፥
ለዘለዓለሙ በደስታ ይዘምሩ፥ እነርሱንም ትጠብቃቸዋለህ፥
ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይደሰቱ።
13አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፥
አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ