መዝሙረ ዳዊት 53
53
1ለመዘምራን አለቃ፥ በማኽላት፥ የዳዊት ትምህርት።
2 #
መዝ. 14፥1-5። ኣላዋቂ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል።
ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፥
በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።#መዝ. 10፥4፤ 36፥2፤ ኢሳ. 32፥6፤ ኤር. 5፥12፤ ሮሜ 3፥10-12።
3 #
መዝ. 11፥4፤ 102፥20። የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ
እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
4 #
መዝ. 12፥2። ሁሉም በደሉ፥ አብረውም ረከሱ፥
አንድ እንኳ በጎን ነገር የሚያደርጋት የለም።
5 #
መዝ. 27፥2፤ መዝ. 79፥6፤ ኢሳ. 9፥11። እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉ
ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁምን?
እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
6በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅጉን ፈሩ፥
እግዚአብሔር የከበቡህን አጥንቶች በትኖአልና፥
እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና አሳፈርሃቸው።
7 #
መዝ. 85፥2። መድኃኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን በሰጠ!
እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥
ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 53: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 53
53
1ለመዘምራን አለቃ፥ በማኽላት፥ የዳዊት ትምህርት።
2 #
መዝ. 14፥1-5። ኣላዋቂ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል።
ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፥
በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።#መዝ. 10፥4፤ 36፥2፤ ኢሳ. 32፥6፤ ኤር. 5፥12፤ ሮሜ 3፥10-12።
3 #
መዝ. 11፥4፤ 102፥20። የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ
እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
4 #
መዝ. 12፥2። ሁሉም በደሉ፥ አብረውም ረከሱ፥
አንድ እንኳ በጎን ነገር የሚያደርጋት የለም።
5 #
መዝ. 27፥2፤ መዝ. 79፥6፤ ኢሳ. 9፥11። እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉ
ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁምን?
እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
6በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅጉን ፈሩ፥
እግዚአብሔር የከበቡህን አጥንቶች በትኖአልና፥
እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና አሳፈርሃቸው።
7 #
መዝ. 85፥2። መድኃኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን በሰጠ!
እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥
ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።