የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 56

56
1 # 1ሳሙ. 21፥10። ለመዘምራን አለቃ፥ ከቅዱሳን ስለ ራቁ ሕዝብ፥ ፍልስጥኤማውያን በጋት በያዙት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
2አቤቱ፥ ሰው ረግጦኛልና ማረኝ፥
ሁልጊዜም ተዋጊ አስጨንቆኛል።
3የሚዋጉኝ በዝተዋልና
ቀኑን ሁሉ ጠላቶቼ ረገጡኝ።
4እኔ ግን ፈራሁ በአንተም ታመንሁ።
5 # መዝ. 118፥6፤ ዕብ. 13፥6፤ መዝ. 130፥5። በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ፥
በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሥጋ#56፥5ሰው ምን ያደርገኛል?
6ሁልጊዜ ቃሎቼን ይጠመዝዙብኛል፥
በእኔ ላይም የሚመክሩት ሁሉ ለክፉ ነው።
7 # መዝ. 140፥5-6። ይሸምቁብኛል ይሸሸጋሉ፥
ተረከዜን ይከታተላሉ፥
ነፍሴንም ለማጥፋት ይጠብቃሉ።
8መቼም አታድናቸውም!
አቤቱ አሕዛብን በቁጣ ጣላቸው።
9 # መዝ. 10፥14፤ 2ነገ. 20፥5፤ ኢሳ. 25፥8፤ ራእ. 7፥17። አምላክ ሆይ፥ መዋተቴን ነገርሁህ፥
እንባዬን በአቁማዳ ውስጥ አኑር።
10በጠራሁህ ጊዜ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፥
አንተ አምላኬ ከእኔ ጋር እንደሆንህ እነሆ፥ አወቅሁ።
11በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ፥
በጌታ ቃሉን እወድሳለሁ።
12በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?
13 # ዘኍ. 30፥3። አቤቱ፥ በአንተ ዘንድ ሰእለት አለብኝ፥ የምስጋና መሥዋዕት አቀርብልሀለሁ፥
14ነፍሴን ከሞት፥ እግሮቼን ከመውደቅ አድነሃልና፥
በሕያዋን ብርሃን በእግዚአብሔር ዘንድ እመላለስ ዘንድ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ