መዝሙረ ዳዊት 57
57
1 #
1ሳሙ. 22፥1። ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
2 #
መዝ. 17፥8፤ 36፥8። ማረኝ፥ አቤቱ፥ ማረኝ፥
ነፍሴ አንተን ታምናለችና፥
ጉዳት እስኪያልፍ ድረስ
በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ።
3እቅዱን በእኔ ላይ ወደሚፈጽመው አምላክ
ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጮኻለሁ።
4ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥
ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፥
እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነቱን ላከ።
5 #
መዝ. 11፥2፤ 64፥4፤ 17፥11-12፤ 22፥22፤ 58፥7። ነፍሴን ከአንበሶች መካከል አዳናት።
ደንግጬ ተኛሁ፥
የሰው ልጆች ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ፥
አንደበታቸው የተሳለ ሾተል ነው።
6 #
መዝ. 72፥19፤ ዘኍ. 14፥21። አምላክ ሆይ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፥
ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።
7 #
መዝ. 7፥15፤ 9፥16-17፤ 140፥5-6። ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ፥
ነፍሴንም አጐበጡአት፥
ጉድጓድ በፊቴ ቈፈሩ፥ በእርሱም ወደቁ።
8 #
መዝ. 108፥2። ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው፥
እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።
9 #
ኢዮብ 38፥12። ክብሬ ይነሣ#57፥9 ልነሣሣ፥
በገናና መሰንቆም ይነሡ፥
እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
10 #
መዝ. 9፥12፤ 18፥50። አቤቱ፥ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥
በወገኖችም ዘንድ እዘምርልሃለሁ፥
11 #
መዝ. 36፥6፤ 71፥19። ርኅራኄህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላለችና፥
እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ።
12አምላክ ሆይ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፥
ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 57: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ