መዝሙረ ዳዊት 58
58
1ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። የዳዊት ቅኔ።
2 #
መዝ. 82፥2፤ ዘዳ. 16፥19። በእውነት ጽድቅን ትናገራላችሁን፥
ገዢዎች ሆይ፥ በቅን ትፈርዳላችሁን?
3በልባችሁ በምድር ላይ ግፍን ትሠራላችሁና፥
እጆቻችሁም ዐመጽን ይፈጽማሉና።
4ክፉዎች ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፥
ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ።
5 #
መዝ. 64፥4፤ 140፥3፤ ሮሜ 3፥13። የእባብ መርዝ ዓይነት መርዝ አላቸው፥
ጆሮውን እንደደፈነ እባብ ናቸው፥
6አስማተኛ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ።
7 #
መዝ. 3፥7። አምላክ ሆይ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፥
የአንበሶቹን መንጋጋቸውን አድቅቅ።
8 #
መዝ. 37፥2፤ ጥበ. 16፥29። እንደሚፈስስ ውኃ ይጥፉ፥
ቀስትን ሲገትሩ ፍላጻው ይጣመም።#58፥8 አንዳንድ እትሞች “እንደ ሣር ተረግጠው ይጠውልጉ” የሚል ትርጒም ያቀርባሉ
9 #
ኢዮብ 3፥16። እንደሚሟሟ ቀንድ አውጣ፥
ፀሐይን እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ።
10 #
ኢዮብ 21፥18፤ ሆሴዕ 13፥3፤ ናሆም 1፥10። ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥
ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።
11 #
መዝ. 68፥24፤ ኢሳ. 63፥1-6። ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፥
በክፉዉም ደም እግሮቹን ይታጠባል።
12ሰውም፦ “በእውነት ለጻድቅ ፍሬ አለው፥
በእውነት በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 58: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ