መዝሙረ ዳዊት 59
59
1 #
1ሳሙ. 19፥11። ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ሳኦል ይገድሉት ዘንድ ቤቱን እንዲጠብቁ በላከ ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
2አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶቼ አድነኝ፥
በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ።
3ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥
ከደም ሰዎችም አድነኝ።
4እነሆ፥ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፥
ብርቱዎችም በላዬ ተሰበሰቡ፥
አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኃጢአቴም አይደለም።
5ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፥
ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም።
6አንተም አቤቱ፥ የኃያላን አምላክ፥ የእስራኤል አምላክ፥
አሕዛብን ሁሉ ትጐበኛቸው ዘንድ ተነሥ፥
ክፉ ከዳተኞችን ሁሉ አትማራቸው።
7 #
መዝ. 55፥11። ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ያላዝኑ፥
በከተማም ይዙሩ።
8እነሆ፥ በአፋቸው ግሳት ይናገራሉ፥
ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፥
ማን ይሰማል? ይላሉ።
9 #
መዝ. 2፥4፤ 37፥13፤ ጥበ. 4፥18። አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥
አሕዛብንም ሁሉ ማላገጫ ታደርጋቸዋለህ።
10እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነውና
ኃይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ።
11የአምላኬ ቸርነቱ ይገናኘኛል
አምላኬ በጠላቶቼ ላይ ያሳየኛል።
12ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፥
አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም።
13 #
ምሳ. 12፥13፤ 18፥7። ስለ አፋቸው ኃጢአት ስለ ከንፈራቸውም ቃል፥
መርገምንና ሐሰትን ስለሚናገሩ፥
በትዕቢታቸው ይጠመዱ።
14 #
መዝ. 83፥18-19፤ ሕዝ. 5፥13። በቁጣ አጥፋቸው፥ እንዳይኖሩም አጥፋቸው፥
የያዕቆብም አምላክ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንደሚገዛ ይወቁ።
15ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ።
16እነርሱም መብል ለመፈለግ ይበተኑ፥
ያልጠገቡ እንደሆነም ያላዝኑ።
17እኔ ግን ለኃይልህ እቀኛለሁ፥
በምሕረትህም ማልዶ ደስ ይለኛል፥
በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና አምባዬ ሆነኸኛልና።
18ረዳቴ ሆይ፥ ለአንተ ለአምላኬ እዘምራለሁ፥
አንተ፥ አምላኬ፥ መጠጊያዬ የቸርነትም አምላኬ ነህና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 59: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 59
59
1 #
1ሳሙ. 19፥11። ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ሳኦል ይገድሉት ዘንድ ቤቱን እንዲጠብቁ በላከ ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
2አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶቼ አድነኝ፥
በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ።
3ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥
ከደም ሰዎችም አድነኝ።
4እነሆ፥ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፥
ብርቱዎችም በላዬ ተሰበሰቡ፥
አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኃጢአቴም አይደለም።
5ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፥
ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም።
6አንተም አቤቱ፥ የኃያላን አምላክ፥ የእስራኤል አምላክ፥
አሕዛብን ሁሉ ትጐበኛቸው ዘንድ ተነሥ፥
ክፉ ከዳተኞችን ሁሉ አትማራቸው።
7 #
መዝ. 55፥11። ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ያላዝኑ፥
በከተማም ይዙሩ።
8እነሆ፥ በአፋቸው ግሳት ይናገራሉ፥
ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፥
ማን ይሰማል? ይላሉ።
9 #
መዝ. 2፥4፤ 37፥13፤ ጥበ. 4፥18። አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥
አሕዛብንም ሁሉ ማላገጫ ታደርጋቸዋለህ።
10እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነውና
ኃይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ።
11የአምላኬ ቸርነቱ ይገናኘኛል
አምላኬ በጠላቶቼ ላይ ያሳየኛል።
12ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፥
አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም።
13 #
ምሳ. 12፥13፤ 18፥7። ስለ አፋቸው ኃጢአት ስለ ከንፈራቸውም ቃል፥
መርገምንና ሐሰትን ስለሚናገሩ፥
በትዕቢታቸው ይጠመዱ።
14 #
መዝ. 83፥18-19፤ ሕዝ. 5፥13። በቁጣ አጥፋቸው፥ እንዳይኖሩም አጥፋቸው፥
የያዕቆብም አምላክ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንደሚገዛ ይወቁ።
15ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ።
16እነርሱም መብል ለመፈለግ ይበተኑ፥
ያልጠገቡ እንደሆነም ያላዝኑ።
17እኔ ግን ለኃይልህ እቀኛለሁ፥
በምሕረትህም ማልዶ ደስ ይለኛል፥
በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና አምባዬ ሆነኸኛልና።
18ረዳቴ ሆይ፥ ለአንተ ለአምላኬ እዘምራለሁ፥
አንተ፥ አምላኬ፥ መጠጊያዬ የቸርነትም አምላኬ ነህና።