የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 57

57
1 # 1ሳሙ. 22፥1። ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
2 # መዝ. 17፥8፤ 36፥8። ማረኝ፥ አቤቱ፥ ማረኝ፥
ነፍሴ አንተን ታምናለችና፥
ጉዳት እስኪያልፍ ድረስ
በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ።
3እቅዱን በእኔ ላይ ወደሚፈጽመው አምላክ
ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጮኻለሁ።
4ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥
ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፥
እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነቱን ላከ።
5 # መዝ. 11፥2፤ 64፥4፤ 17፥11-12፤ 22፥22፤ 58፥7። ነፍሴን ከአንበሶች መካከል አዳናት።
ደንግጬ ተኛሁ፥
የሰው ልጆች ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ፥
አንደበታቸው የተሳለ ሾተል ነው።
6 # መዝ. 72፥19፤ ዘኍ. 14፥21። አምላክ ሆይ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፥
ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።
7 # መዝ. 7፥15፤ 9፥16-17፤ 140፥5-6። ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ፥
ነፍሴንም አጐበጡአት፥
ጉድጓድ በፊቴ ቈፈሩ፥ በእርሱም ወደቁ።
8 # መዝ. 108፥2። ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው፥
እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።
9 # ኢዮብ 38፥12። ክብሬ ይነሣ#57፥9 ልነሣሣ
በገናና መሰንቆም ይነሡ፥
እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
10 # መዝ. 9፥12፤ 18፥50። አቤቱ፥ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥
በወገኖችም ዘንድ እዘምርልሃለሁ፥
11 # መዝ. 36፥6፤ 71፥19። ርኅራኄህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላለችና፥
እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ።
12አምላክ ሆይ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፥
ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ