መዝሙረ ዳዊት 69
69
1ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ የዳዊት መዝሙር።
2 #
መዝ. 18፥5፤ 93፥3-4፤ ኢዮብ 22፥11። አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ#69፥2 አንገቴ። ደርሶብኛልና አድነኝ።
3በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቆሚያም የለኝም።
ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ።
4በጩኸት ደከምሁ ጉሮሮዬም ሰለለ፥
አምላኬን ስጠብቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።
5 #
መዝ. 35፥19፤ ዮሐ. 15፥25። በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፥
በዓመፅ ያሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ፥
በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ።
6አቤቱ፥ አንተ ቅብጠቴን ታውቃለህ፥
ጥፋቴም ከአንተ አልተሰወረም።
7አቤቱ የሠራዊት አምላክ፥ ተስፋ የሚያደርጉህ በእኔ አይፈሩ፥
የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ የሚሹህ በእኔ አይነወሩ።
8ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፥
እፍረትም ፊቴን ሸፍናለችና።
9ለወንድሞቼ እንደ ሌላ፥
ለእናቴ ልጆችም እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።
10 #
ዮሐ. 2፥17፤
ሮሜ 15፥3። የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
11ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥
ለስድብም ሆነብኝ።
12ማቅ ለበስሁ ምሳሌም#69፥12 መቀለጃ፥ መተረቻ። ሆንሁላቸው።
13በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ፥
ሰካራሞች በእኔ ላይ ይዘፍናሉ።
14አቤቱ፥ በመልካሙ ጊዜ ጸሎቴ ወደ አንተ ነው፥
አቤቱ፥ በቸርነትህ ብዛት በማዳንህም እውነት አድምጠኝ።
15እንዳይውጠኝ ከረግረግ አውጣኝ፥
ከሚጠሉኝና ከጥልቅ ውኃ አስጥለኝ።
16የውኃው ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥
ጉድጓድም አፉን በእኔ ላይ አይዝጋ።
17አቤቱ፥ ቸርነትህ መልካም ናትና ስማኝ።
እንደ ርኅራኄህም ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፥
18ከባርያህም ፊትህን አትሰውር፥
ተጨንቄአለሁና ፈጥነህ መልስልኝ።
19ወደ ነፍሴ ቀርበህ ተቤዣት፥
ስለ ጠላቶቼም አድነኝ።
20አንተ ስድቤን እፍረቴንም ነውሬንም ታውቃለህ፥
የሚያስጨንቁኝ ሁሉ በፊትህ ናቸው።
21ስድብ እስክታመም ድረስ ልቤን ሰበረው፥
አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም፥
የሚያጽናናኝም አጣሁ።
22 #
ማቴ. 27፥48፤ ማር. 15፥36፤ ሉቃ. 23፥26፤ ዮሐ. 19፥28፤29። ለመብሌ ሐሞት#69፥22 ቃል በቃል “መርዝ” ማለት ነው። ሰጡኝ፥
ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ።
23 #
ሮሜ 11፥9፤10። ማዕዳቸው በፊታቸው
ለወጥመድ ለፍዳ ለዕንቅፋት ትሁንባቸው፥
24ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥
ወገባቸውም ዘወትር ይንቀጥቀጥ።
25መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥
የቁጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው።
26 #
የሐዋ. 1፥20። ማደሪያቸው በረሃ ትሁን፥
በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፥
27አንተ የቀሠፍኸውን እነርሱ አሳድደዋልና፥
ባቈሰልከውም ላይ ጥዝጣዜ ጨመሩ።
28በበደል ላይ በደልን ጨምርባቸው፥
በጽድቅህም አይግቡ።
29 #
ዘፀ. 32፥32፤ ራእ. 3፥5፤ 13፥8፤ 17፥8። ከሕያዋን መጽሐፍ ይደምሰሱ፥
ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።
30እኔ ችግረኛና ቁስለኛ ነኝ፥
አቤቱ፥ መድኃኒትህ ያቁመኝ።
31የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አመሰግናለሁ፥
በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
32ቀንድና ሰኰና ካበቀለ ኰርማ ወይም ወይፈን ይልቅ
ጌታን ደስ ያሰኘዋል።
33ችግረኞች ያያሉ ደስ ይላቸዋል፥
እግዚአብሔርን ፈልጉ ሕያዋንም ሁኑ።
34ጌታ ችግረኞችን ሰምቶአልና፥
እስረኞቹንም አልናቀምና።
35ሰማይና ምድር ባሕርም
በእርሷም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመሰግኑታል።
36እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፥
የይሁዳንም ከተሞች ይሠራልና፥
በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሱአትማል።
37የአገልጋዮቹ ልጆች ይኖሩባታል፥
ስሙንም የሚወድዱ በዚያ ይቀመጣሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 69: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 69
69
1ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ የዳዊት መዝሙር።
2 #
መዝ. 18፥5፤ 93፥3-4፤ ኢዮብ 22፥11። አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ#69፥2 አንገቴ። ደርሶብኛልና አድነኝ።
3በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቆሚያም የለኝም።
ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ።
4በጩኸት ደከምሁ ጉሮሮዬም ሰለለ፥
አምላኬን ስጠብቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።
5 #
መዝ. 35፥19፤ ዮሐ. 15፥25። በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፥
በዓመፅ ያሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ፥
በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ።
6አቤቱ፥ አንተ ቅብጠቴን ታውቃለህ፥
ጥፋቴም ከአንተ አልተሰወረም።
7አቤቱ የሠራዊት አምላክ፥ ተስፋ የሚያደርጉህ በእኔ አይፈሩ፥
የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ የሚሹህ በእኔ አይነወሩ።
8ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፥
እፍረትም ፊቴን ሸፍናለችና።
9ለወንድሞቼ እንደ ሌላ፥
ለእናቴ ልጆችም እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።
10 #
ዮሐ. 2፥17፤
ሮሜ 15፥3። የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
11ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥
ለስድብም ሆነብኝ።
12ማቅ ለበስሁ ምሳሌም#69፥12 መቀለጃ፥ መተረቻ። ሆንሁላቸው።
13በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ፥
ሰካራሞች በእኔ ላይ ይዘፍናሉ።
14አቤቱ፥ በመልካሙ ጊዜ ጸሎቴ ወደ አንተ ነው፥
አቤቱ፥ በቸርነትህ ብዛት በማዳንህም እውነት አድምጠኝ።
15እንዳይውጠኝ ከረግረግ አውጣኝ፥
ከሚጠሉኝና ከጥልቅ ውኃ አስጥለኝ።
16የውኃው ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥
ጉድጓድም አፉን በእኔ ላይ አይዝጋ።
17አቤቱ፥ ቸርነትህ መልካም ናትና ስማኝ።
እንደ ርኅራኄህም ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፥
18ከባርያህም ፊትህን አትሰውር፥
ተጨንቄአለሁና ፈጥነህ መልስልኝ።
19ወደ ነፍሴ ቀርበህ ተቤዣት፥
ስለ ጠላቶቼም አድነኝ።
20አንተ ስድቤን እፍረቴንም ነውሬንም ታውቃለህ፥
የሚያስጨንቁኝ ሁሉ በፊትህ ናቸው።
21ስድብ እስክታመም ድረስ ልቤን ሰበረው፥
አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም፥
የሚያጽናናኝም አጣሁ።
22 #
ማቴ. 27፥48፤ ማር. 15፥36፤ ሉቃ. 23፥26፤ ዮሐ. 19፥28፤29። ለመብሌ ሐሞት#69፥22 ቃል በቃል “መርዝ” ማለት ነው። ሰጡኝ፥
ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ።
23 #
ሮሜ 11፥9፤10። ማዕዳቸው በፊታቸው
ለወጥመድ ለፍዳ ለዕንቅፋት ትሁንባቸው፥
24ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥
ወገባቸውም ዘወትር ይንቀጥቀጥ።
25መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥
የቁጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው።
26 #
የሐዋ. 1፥20። ማደሪያቸው በረሃ ትሁን፥
በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፥
27አንተ የቀሠፍኸውን እነርሱ አሳድደዋልና፥
ባቈሰልከውም ላይ ጥዝጣዜ ጨመሩ።
28በበደል ላይ በደልን ጨምርባቸው፥
በጽድቅህም አይግቡ።
29 #
ዘፀ. 32፥32፤ ራእ. 3፥5፤ 13፥8፤ 17፥8። ከሕያዋን መጽሐፍ ይደምሰሱ፥
ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።
30እኔ ችግረኛና ቁስለኛ ነኝ፥
አቤቱ፥ መድኃኒትህ ያቁመኝ።
31የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አመሰግናለሁ፥
በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
32ቀንድና ሰኰና ካበቀለ ኰርማ ወይም ወይፈን ይልቅ
ጌታን ደስ ያሰኘዋል።
33ችግረኞች ያያሉ ደስ ይላቸዋል፥
እግዚአብሔርን ፈልጉ ሕያዋንም ሁኑ።
34ጌታ ችግረኞችን ሰምቶአልና፥
እስረኞቹንም አልናቀምና።
35ሰማይና ምድር ባሕርም
በእርሷም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመሰግኑታል።
36እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፥
የይሁዳንም ከተሞች ይሠራልና፥
በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሱአትማል።
37የአገልጋዮቹ ልጆች ይኖሩባታል፥
ስሙንም የሚወድዱ በዚያ ይቀመጣሉ።