መዝሙረ ዳዊት 72
72
1ስለ ሰሎሞን።
2 #
መዝ. 99፥4፤ ኤር. 23፥5፤ ምሳ. 31፥8-9። አቤቱ፥ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ፥
ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ፥
ሕዝብህን በጽድቅ፥
ችግረኞችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ።
3 #
ኢሳ. 52፥7፤ 55፥12። በጽድቅ፥ ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ።
4ለችግረኞች ሕዝብ በጽድቅ ይፍረድ፥
የድሆችንም ልጆች ያድን፥
ጨቋኙንም ይጨፍልቅ።
5 #
መዝ. 89፥37-38፤ ኤር. 31፥35። ፀሐይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ፥
በጨረቃም ፊት ለፊት ለልጅ ልጅ ይኑር።
6 #
ዘዳ. 32፥2፤ ኢሳ. 45፥8፤ ሆሴዕ 6፥3። እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ፥
በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይውረድ።
7በዘመኑም ጽድቅ ያብብ፥
ጨረቃም እስኪያልፍ ድረስ ሰላም ይብዛ።
8 #
ዘዳ. 11፥24፤ ዘካ. 9፥10፤ ሲራ. 44፥21። ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥
ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይግዛ።
9 #
ኢሳ. 49፥23፤ ሚክ. 7፥17። በፊቱም የኢትዮጵያ ሰዎች#72፥9 ዕብራይስጡ “የምድረ በዳ ሰዎች” ይላል። ይሰግዳሉ፥
ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።
10 #
መዝ. 68፥30፤ ኢሳ. 60፥5-6፤ 1ነገ. 10፥1። የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፥
የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ።
11 #
መዝ. 47፥8። ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል።
አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል።
12ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፥
ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።
13 #
ምሳ. 31፥9። ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፥
የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል።
14ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸውን ያድናል፥
ደማቸው#72፥14 ግሪኩ “ስማቸው” ይላል። በፊቱ ክቡር ነው።
15በሐወት ይኑር፥ ከዓረብም ወርቅ ይሰጠው፥
ሁልጊዜም ስለ እርሱ ይጸልይ፥
ዘወትርም ይባረክ።
16 #
ኢሳ. 27፥6፤ ሆሴዕ 14፥6-8፤ አሞጽ 9፥13። በምድር ላይ እህሉ ይትረፍረፍ፥ በተራሮችም ላይ ሰብል ይወዛወዝ፥
ፍሬውም እንደ ሊባኖስ ከፍ ከፍ ይበል፥
ሰዎችም በከተማ እንደ ምድር ሣር ይለምልሙ።
17 #
ዘፍ. 12፥3፤ 22፥18፤ 26፥4፤ መዝ. 21፥7፤ ዘካ. 8፥13። ስሙ ለዘለዓለም ይታወስ፥
እንደ ፀሐይ ዕድሜ ስሙ ጸንቶ ይኑር፥
የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሱ ይባረኩ፥
አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑት፥
18 #
መዝ. 41፥14፤ 89፥53፤ 106፥48፤ 136፥4። ብቻውን ተኣምራትን የሚያደርግ
የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።
19 #
መዝ. 57፥5፤ ዘኍ. 14፥21። የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፥
ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ።
አሜን፥ አሜን።
20የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎቶች#72፥20 ግሪኩ “መዝሙር” ይላል። ተፈጸሙ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 72: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ