መዝሙረ ዳዊት 73
73
1የአሳፍ መዝሙር።
እግዚአብሔር ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው፥
ልባቸው ንጹሕ ለሆነ።
2እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥
በአረማመዴም ልወድቅ ትንሽ ቀረኝ።
3 #
መዝ. 37፥1፤ ኢዮብ 21፥13። የክፉዎችን ሰላም አይቼ
በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
4ለሞታቸው#73፥4 “እስከ ሞታቸው ድረስ አይሰቃዩም” ብለው የሚተረጉሙ አሉ፤ “ሞት” የሚለውን ቃል ሳያስገቡም “ስቃይ የለባቸውም” ብለው የሚተረጉሙም አሉ። ስቃይ የለውምና፥
ሰውነታቸውም ጤናማ ነው።
5እንደ ሰው በድካም አልሆኑም፥
ከሰው ጋርም አልተገረፉም።
6ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ሐብላቸው፥
ዓመጽ መጐናጸፊያቸው ሆነ።
7 #
ኢዮብ 15፥27። ዓይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ፥
ልባቸውም በቅዥት ተሞላ።
8 #
መዝ. 17፥10። በሹፈት ክፉ ነገርን ተናገሩ።
ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ።
9በሰማይ ላይ በድፍረት ተናገሩ፥
አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ።
10ስለዚህ ሕዝቤም ወደ እነርሱ ይመለሳሉ፥
ከሞላ ውሃቸውም ይጋታሉ#73፥10 የሚቀርብላቸውን መጥፎ ምክር በሙሉ ይቀበላሉ።፥
11 #
መዝ. 10፥11፤ ኢዮብ 22፥13። እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል?
በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለን? ይላሉ።
12እነሆ፥ እነዚህ ክፉዎቸ ይደሰታሉ፥
ሁልጊዜም ሀብታቸውን ያበዛሉ።
13 #
መዝ. 26፥6፤ ሚል. 3፥14። እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥
እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።
14ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥
መሰደቤም በማለዳ ነው።
15“እንደዚህ እናገራለሁ” ብል ኖሮ፥
እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር።
16አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥
ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ።
17ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥
ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ።
18በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፥
ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው።
19እንዴት ለጥፋት ሆኑ!
በድንገት አለቁ፥ በድንጋጤ ጠፉ።
20 #
ኢዮብ 20፥8። ከሕልም እንደሚነቃ፥
አቤቱ፥ ስትነቃ መልካቸውን ትንቃለህ።
21ልቤ ነድዶአልና፥ ኩላሊቴም ቀልጦአልና፥
22እኔ የተናቅሁ ነኝ አላወቅሁምም፥
በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
23 #
መዝ. 121፥5። እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥
ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ።
24በአንተ ምክር መራኸኝ፥
ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።
25በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ?
በምድርስ ከአንተ ጋር ሆኜ ሌላ ምን እሻለሁ?
26ልቤና ሥጋዬ አለቀ፥
እግዚአብሔር ግን ዘለዓለም የልቤ ኃይልና እድል ፈንታዬ ነው።
27እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፥
በማመንዘር ከአንተ የሚርቁትን#73፥27 በዚህ ጥቅስ ማመንዘር ለእግዚአብሔር የነበረን ታማኝነት ማጉደል ማለት ነው። ሁሉ አጠፋኻቸው።
28ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፥
መጠለያዬም ጌታ ነው
ሥራህን ሁሉ እናገር ዘንድ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 73: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 73
73
1የአሳፍ መዝሙር።
እግዚአብሔር ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው፥
ልባቸው ንጹሕ ለሆነ።
2እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥
በአረማመዴም ልወድቅ ትንሽ ቀረኝ።
3 #
መዝ. 37፥1፤ ኢዮብ 21፥13። የክፉዎችን ሰላም አይቼ
በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
4ለሞታቸው#73፥4 “እስከ ሞታቸው ድረስ አይሰቃዩም” ብለው የሚተረጉሙ አሉ፤ “ሞት” የሚለውን ቃል ሳያስገቡም “ስቃይ የለባቸውም” ብለው የሚተረጉሙም አሉ። ስቃይ የለውምና፥
ሰውነታቸውም ጤናማ ነው።
5እንደ ሰው በድካም አልሆኑም፥
ከሰው ጋርም አልተገረፉም።
6ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ሐብላቸው፥
ዓመጽ መጐናጸፊያቸው ሆነ።
7 #
ኢዮብ 15፥27። ዓይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ፥
ልባቸውም በቅዥት ተሞላ።
8 #
መዝ. 17፥10። በሹፈት ክፉ ነገርን ተናገሩ።
ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ።
9በሰማይ ላይ በድፍረት ተናገሩ፥
አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ።
10ስለዚህ ሕዝቤም ወደ እነርሱ ይመለሳሉ፥
ከሞላ ውሃቸውም ይጋታሉ#73፥10 የሚቀርብላቸውን መጥፎ ምክር በሙሉ ይቀበላሉ።፥
11 #
መዝ. 10፥11፤ ኢዮብ 22፥13። እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል?
በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለን? ይላሉ።
12እነሆ፥ እነዚህ ክፉዎቸ ይደሰታሉ፥
ሁልጊዜም ሀብታቸውን ያበዛሉ።
13 #
መዝ. 26፥6፤ ሚል. 3፥14። እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥
እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።
14ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥
መሰደቤም በማለዳ ነው።
15“እንደዚህ እናገራለሁ” ብል ኖሮ፥
እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር።
16አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥
ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ።
17ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥
ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ።
18በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፥
ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው።
19እንዴት ለጥፋት ሆኑ!
በድንገት አለቁ፥ በድንጋጤ ጠፉ።
20 #
ኢዮብ 20፥8። ከሕልም እንደሚነቃ፥
አቤቱ፥ ስትነቃ መልካቸውን ትንቃለህ።
21ልቤ ነድዶአልና፥ ኩላሊቴም ቀልጦአልና፥
22እኔ የተናቅሁ ነኝ አላወቅሁምም፥
በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
23 #
መዝ. 121፥5። እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥
ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ።
24በአንተ ምክር መራኸኝ፥
ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።
25በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ?
በምድርስ ከአንተ ጋር ሆኜ ሌላ ምን እሻለሁ?
26ልቤና ሥጋዬ አለቀ፥
እግዚአብሔር ግን ዘለዓለም የልቤ ኃይልና እድል ፈንታዬ ነው።
27እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፥
በማመንዘር ከአንተ የሚርቁትን#73፥27 በዚህ ጥቅስ ማመንዘር ለእግዚአብሔር የነበረን ታማኝነት ማጉደል ማለት ነው። ሁሉ አጠፋኻቸው።
28ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፥
መጠለያዬም ጌታ ነው
ሥራህን ሁሉ እናገር ዘንድ።