የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 75

75
1ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
2አቤቱ፥ እናመሰግንሃለን
እናመሰግንሃለን፥ ስምህም ቅርብ ነው፥
ተኣምራትህን ሁሉ እንናገራለን።
3“በወሰንኩት ጊዜ እኔ በቅን እፈርዳለሁ።”#75፥3 የዚህ ዐረፍተ ነገር ባለቤት እግዚአብሔር ነው።
4 # መዝ. 46፥3፤ 60፥4፤ 93፥1፤ 96፥10፤ 104፥5፤ 1ሳሙ. 2፥8፤ ኢሳ. 24፥19። ምድርና በእርሷ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ ይናወጣሉ፥
እኔም ምሰሶችዋን አጠናሁ።
5 # 1ሳሙ. 2፥3፤ ዘካ. 2፥1-4። ትምክህተኞችን፦ “አትኩሩ፥
ክፉዎችንም፦ ቀንዳችሁን አታንሡ#75፥5 አትታበዩ።፥” አልኋቸው
6 # ኢዮብ 15፥25። ቀንዳችሁን እስከ ላይ አታንሡ፥
በእብሪተኛ አንገት አትናገሩ።
7 # ማቴ. 24፥23-27። ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረበዳ የለምና፥
8 # ኢዮብ 5፥11፤ 1ሳሙ. 2፥7። እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና
ይህንን ያዋርዳል ያንንም ያከብራል።
9 # መዝ. 60፥5፤ ኢዮብ 21፥20፤ ኢሳ. 51፥17፤21-22፤ ኤር. 25፥15፤ ዕን. 2፥16። ጽዋ በጌታ እጅ ነውና፥
ኃይለኛ የወይን ጠጅ ሞላበት፥
ከዚህ ወደዚያ አገላበጠው፥
ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም፥
የምድር ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል።
10እኔ ግን ለዘለዓለም ደስ ይለኛል፥
ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬን አቀርባለሁ።
11 # መዝ. 92፥11። “የክፉዎችን ቀንዶች#75፥11 ኃይል። ሁሉ እሰብራለሁ፥
የጻድቃን ቀንዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ