መዝሙረ ዳዊት 80
80
1ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ ስለ አሦራውያን፥ የአሳፍ የምስክር መዝሙር።
2 #
መዝ. 23፥1-3፤ 95፥7፤ 100፥3፤ ዘፍ. 48፥15፤ ዘፀ. 25፥22፤ 1ሳሙ. 4፥4፤ 2ሳሙ. 6፥2፤ ሚክ. 7፥14። ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥
የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፥
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ብርሃንህን አብራ።
3በኤፍሬምና በብንያም በምናሴም
ኃይልህን አንሣ እኛንም ለማዳን ና።
4 #
መዝ. 4፥7፤ 31፥17፤ 67፥2፤ 85፥5፤ ዘኍ. 6፥25፤ ዳን. 9፥17። አቤቱ፥ መልሰን፥
ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
5 #
መዝ. 13፥2፤ 44፥24፤ 74፥1፤ 79፥5፤ 89፥47፤ ዘዳ. 4፥24። የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥
በሕዝብህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለህ?
6 #
መዝ. 42፥4፤ 102፥10። የእንባ እንጀራን መገብካቸው፥
እንባም በስፍር አጠጣሃቸው።
7 #
መዝ. 44፥14፤ 79፥4፤ 123፥3-4፤ ኢዮብ 12፥4፤ ዳን. 9፥16፤ ሶፎ. 2፥8። ለጎረቤቶቻችን መከራከርያ አደረግኸን፥
ጠላቶቻችንም ይሣለቁብናል።
8የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥
ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
9ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ፥
አሕዛብን አባረርህ እርሷንም ተከልህ።
10በፊትዋም ስፍራን አዘጋጀህ፥
ሥሮችዋንም ተከልህ ምድርንም ሞላች።
11ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥
ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ።
12ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባሕር፥
ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።
13 #
መዝ. 89፥41። አጥርዋን ለምን አፈረስህ?
መንገድ አላፊም ሁሉ ይቀጥፋታል።
14 #
ሆሴዕ 2፥14። የዱር እርያ አረከሳት፥
የአገር አውሬም ተሰማራባት።
15የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ እንግዲህ ተመለስ፥
ከሰማይ ተመልከት፥ እይም፥
ይህችንም የወይን ግንድ ጐብኝ።
16ቀኝህ እጅህ የተከለውን፥
ለራስህ ያጸናኸውን ልጅ ጠብቅ።
17በእሳት ተቃጥላለች ተነቅላማለች
ከፊትህ ተግሣጽም የተነሣ ይጠፋሉ።
18እጅህ በቀኝህ ሰው ላይ፥
ለአንተ ባጸናኸው በሰው ልጅ ላይ ትሁን።
19ከአንተም አንራቅ፥
አድነን ስምህንም እንጠራለን።
20የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥
ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 80: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 80
80
1ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ ስለ አሦራውያን፥ የአሳፍ የምስክር መዝሙር።
2 #
መዝ. 23፥1-3፤ 95፥7፤ 100፥3፤ ዘፍ. 48፥15፤ ዘፀ. 25፥22፤ 1ሳሙ. 4፥4፤ 2ሳሙ. 6፥2፤ ሚክ. 7፥14። ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥
የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፥
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ብርሃንህን አብራ።
3በኤፍሬምና በብንያም በምናሴም
ኃይልህን አንሣ እኛንም ለማዳን ና።
4 #
መዝ. 4፥7፤ 31፥17፤ 67፥2፤ 85፥5፤ ዘኍ. 6፥25፤ ዳን. 9፥17። አቤቱ፥ መልሰን፥
ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
5 #
መዝ. 13፥2፤ 44፥24፤ 74፥1፤ 79፥5፤ 89፥47፤ ዘዳ. 4፥24። የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥
በሕዝብህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለህ?
6 #
መዝ. 42፥4፤ 102፥10። የእንባ እንጀራን መገብካቸው፥
እንባም በስፍር አጠጣሃቸው።
7 #
መዝ. 44፥14፤ 79፥4፤ 123፥3-4፤ ኢዮብ 12፥4፤ ዳን. 9፥16፤ ሶፎ. 2፥8። ለጎረቤቶቻችን መከራከርያ አደረግኸን፥
ጠላቶቻችንም ይሣለቁብናል።
8የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥
ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
9ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ፥
አሕዛብን አባረርህ እርሷንም ተከልህ።
10በፊትዋም ስፍራን አዘጋጀህ፥
ሥሮችዋንም ተከልህ ምድርንም ሞላች።
11ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥
ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ።
12ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባሕር፥
ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።
13 #
መዝ. 89፥41። አጥርዋን ለምን አፈረስህ?
መንገድ አላፊም ሁሉ ይቀጥፋታል።
14 #
ሆሴዕ 2፥14። የዱር እርያ አረከሳት፥
የአገር አውሬም ተሰማራባት።
15የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ እንግዲህ ተመለስ፥
ከሰማይ ተመልከት፥ እይም፥
ይህችንም የወይን ግንድ ጐብኝ።
16ቀኝህ እጅህ የተከለውን፥
ለራስህ ያጸናኸውን ልጅ ጠብቅ።
17በእሳት ተቃጥላለች ተነቅላማለች
ከፊትህ ተግሣጽም የተነሣ ይጠፋሉ።
18እጅህ በቀኝህ ሰው ላይ፥
ለአንተ ባጸናኸው በሰው ልጅ ላይ ትሁን።
19ከአንተም አንራቅ፥
አድነን ስምህንም እንጠራለን።
20የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥
ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።