መዝሙረ ዳዊት 9
9
1ለመዘምራን አለቃ፥ በሙትላቤን፥ የዳዊት መዝሙር።
2አቤቱ፥ በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፥
ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።
3እደሰታለሁ፥ በአንተም ሐሤትን አደርጋለሁ፥
ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።
4ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፥
ይሰናከላሉ ከፊትህም ይጠፋሉ።
5ትክክለኛ ፍርድና ዳኝነት አድርገህልኛልና፥
በጽድቅ እየፈረድህ በዙፋንህ ላይ ተቀመጥህ።
6 #
ኢዮብ 18፥17። አሕዛብን ገሠጽህ፥ ክፉዎችንም አጠፋህ፥
ስማቸውንም ለዘለዓለም ደመሰስህ።
7ጠላቶች በጦር ለዘለዓለም ጠፉ፥
ከተሞቻቸውንም አፈረስህ፥
ዝክራቸውም ጠፋ።
8ጌታ ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥
ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ፥
9 #
መዝ. 96፥10፤ 98፥9። እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥
አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል።
10 #
መዝ. 37፥39፤ ኢሳ. 25፥4። ጌታ ለተጨቆኑ መጠጊያ ይሁናቸው፥
በመከራም ጊዜ መሸሸጊያ ይሁንላቸው።
11ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥
አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።
12በጽዮን ለሚኖር ለጌታ ዘምሩ፥
በአሕዛብም መካከል ድንቅ ሥራውን ንገሩ፥
13 #
ኢዮብ 16፥18። ደምን የሚበቀል እርሱ አስቦአልና፥
የድሆችንም#9፥13 ምስኪኖችን፥ የሚሰደዱትን፥ የሚበዘበዙትን፥ ንጹሕ ሳሉ የሚሰቃዩትን ይመለከታል። ጩኸት አልረሳምና።
14 #
ጥበ. 16፥13። አቤቱ፥ እዘንልኝ፥ ጠላቶቼም የሚያመጡብኝን መከራ እይ፥
ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የምታደርገኝ፥
15ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ፥
በጽዮን ልጅ በደጆችዋ
በማዳንህ ደስ ይለኛል።
16አሕዛብ በሠሩት ጉድጓድ ወደቁ፥
በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።
17 #
መዝ. 35፥8፤ ሲራ. 27፥26። ጌታ ተገለጠ፥ ፍርድንም አከናወነ፥
ክፉ በገዛ እጆቹ ሥራ ተጠመደ።
18ክፉዎች ወደ ሲኦል ይመለሳሉ፥
እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም በሙሉ።
19 #
ምሳ. 23፥18። ድሀ ለዘለዓለም አይረሳምና፥
የችግረኞችም ተስፋቸው ለዘለዓለም አይጠፋም።
20አቤቱ፥ ተነሣ፥ ሰውም አይበርታ፥
አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።
21አቤቱ፥ ፍርሃትን በላያቸው አኑር፥
አሕዛብም ደካማ ሰዎች መሆናቸውን ይወቁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 9: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 9
9
1ለመዘምራን አለቃ፥ በሙትላቤን፥ የዳዊት መዝሙር።
2አቤቱ፥ በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፥
ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።
3እደሰታለሁ፥ በአንተም ሐሤትን አደርጋለሁ፥
ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።
4ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፥
ይሰናከላሉ ከፊትህም ይጠፋሉ።
5ትክክለኛ ፍርድና ዳኝነት አድርገህልኛልና፥
በጽድቅ እየፈረድህ በዙፋንህ ላይ ተቀመጥህ።
6 #
ኢዮብ 18፥17። አሕዛብን ገሠጽህ፥ ክፉዎችንም አጠፋህ፥
ስማቸውንም ለዘለዓለም ደመሰስህ።
7ጠላቶች በጦር ለዘለዓለም ጠፉ፥
ከተሞቻቸውንም አፈረስህ፥
ዝክራቸውም ጠፋ።
8ጌታ ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥
ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ፥
9 #
መዝ. 96፥10፤ 98፥9። እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥
አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል።
10 #
መዝ. 37፥39፤ ኢሳ. 25፥4። ጌታ ለተጨቆኑ መጠጊያ ይሁናቸው፥
በመከራም ጊዜ መሸሸጊያ ይሁንላቸው።
11ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥
አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።
12በጽዮን ለሚኖር ለጌታ ዘምሩ፥
በአሕዛብም መካከል ድንቅ ሥራውን ንገሩ፥
13 #
ኢዮብ 16፥18። ደምን የሚበቀል እርሱ አስቦአልና፥
የድሆችንም#9፥13 ምስኪኖችን፥ የሚሰደዱትን፥ የሚበዘበዙትን፥ ንጹሕ ሳሉ የሚሰቃዩትን ይመለከታል። ጩኸት አልረሳምና።
14 #
ጥበ. 16፥13። አቤቱ፥ እዘንልኝ፥ ጠላቶቼም የሚያመጡብኝን መከራ እይ፥
ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የምታደርገኝ፥
15ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ፥
በጽዮን ልጅ በደጆችዋ
በማዳንህ ደስ ይለኛል።
16አሕዛብ በሠሩት ጉድጓድ ወደቁ፥
በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።
17 #
መዝ. 35፥8፤ ሲራ. 27፥26። ጌታ ተገለጠ፥ ፍርድንም አከናወነ፥
ክፉ በገዛ እጆቹ ሥራ ተጠመደ።
18ክፉዎች ወደ ሲኦል ይመለሳሉ፥
እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም በሙሉ።
19 #
ምሳ. 23፥18። ድሀ ለዘለዓለም አይረሳምና፥
የችግረኞችም ተስፋቸው ለዘለዓለም አይጠፋም።
20አቤቱ፥ ተነሣ፥ ሰውም አይበርታ፥
አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።
21አቤቱ፥ ፍርሃትን በላያቸው አኑር፥
አሕዛብም ደካማ ሰዎች መሆናቸውን ይወቁ።