የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 96

96
ከምርኮ በኋላ ቤት በተሠራ ጊዜ
1 # መዝ. 98፥1፤ ኢሳ. 42፥10። ለጌታ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፥
ምድር ሁሉ፥ ለጌታ ዘምሩ።
2ለጌታ ዘምሩ ስሙንም ባርኩ፥
ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ።
3 # መዝ. 98፥4፤ 105፥1። ክብሩን ለአሕዛብ
ተኣምራቱንም ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ፥
4 # መዝ. 48፥2፤ 95፥3፤ 145፥3። ጌታ ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥
ከአማልክትም ሁሉ በላይ የተፈራ ነውና።
5 # መዝ. 97፥7፤ 115፥4-8፤ ኢሳ. 40፥17፤ 1ቆሮ. 8፥4። የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖቶች ናቸውና፥
ጌታ ግን ሰማያትን ሠራ።
6ክብርና ግርማ በፊቱ፥
ኃይልና ውበት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።
7የአሕዛብ ወገኖች፥ ለጌታ አቅርቡ፥
ክብርና ኃይልን ለጌታ አቅርቡ፥
8 # መዝ. 29፥2። ለስሙ የሚገባ ክብርን ለጌታ ስጡ፥
ቁርባን ያዙ፥ ወደ አደባባዮችም ግቡ።
9በቅድስናው ስፍራ ለጌታ ስገዱ፥
ምድር ሁሉ በፊቱ ትናወጥ።
10 # መዝ. 75፥4፤ 93፥1። በአሕዛብ መካከል፦ “ጌታ ነገሠ” በሉ።
እንዳይናወጥም ዓለሙን እርሱ አጸናው፥
አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።
11 # መዝ. 98፥7። ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፥
ባሕርና ሞላዋ ይናወጡ፥
12መስክና በእርሷም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ፥
የዱር ዛፎችም ሁሉ በጌታ ፊት ደስ ይበላቸው፥
13 # መዝ. 98፥9። ይመጣልና፥ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፥
እርሱም ዓለምን በጽድቅ
አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ