የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 98

98
1የዳዊት መዝሙር።
# መዝ. 96፥1፤ ኢሳ. 42፥10፤ 59፥16፤ 63፥5። ለጌታ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፥
ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፥
ቀኙ፥ የተቀደሰ ክንዱም ለእርሱ ማዳን አደረገ።
2ጌታ ማዳኑን አስታወቀ፥
በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ።
3ለእስራኤል ቤት#98፥3 ሰባ ሊቃናት “ለያዕቆብ ምሕረቱን” የሚለውን ሐረግ ይጨምራል። ያለውን
ጽኑ ፍቅርና ታማኝነት አስታወሰ፥
የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን አዩ።
4ምድር ሁሉ ሆይ፥ ለጌታ እልል በሉ፥
በደስታ ፈንድቁ፥ ዘምሩም።
5ለጌታ በመሰንቆ፥
በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ።
6 # መዝ. 47፥6-7። በዋሽንትና በመለከት ድምፅ
በንጉሡ በጌታ ፊት እልል በሉ።
7 # መዝ. 96፥11። ባሕርና ሞላዋ፥
ዓለምም በእርሷም የሚኖሩ ይናወጡ።
8 # ኢሳ. 44፥23፤ 55፥12። ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፥
ተራሮችም በደስታ ይዘምሩ፥
በምድር ሊፈርድ ይመጣልና።
9 # መዝ. 67፥5፤ 96፥13። ዓለምንም በጽድቅ
አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ