መዝሙረ ዳዊት 99
99
1 #
መዝ. 18፥8-11፤ 80፥2፤ 93፥1፤ ዘፀ. 25፥22፤ 1ሳሙ. 4፥4፤ 2ሳሙ. 6፥2። ጌታ ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፥
በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።
2ጌታ በጽዮን ታላቅ ነው፥
እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።
3 #
ኢሳ. 6፥3። ቅዱስ ነውና
ሁሉም ታላቅና ግሩም ስምህን ያመስግኑ።
4 #
መዝ. 72፥1፤ ኤር. 23፥5። ፍርድን የምትወድ ኃያል ንጉሥ፥
አንተ ቅንነትን አጸናህ፥
በያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ ፈጽምህ።
5 #
መዝ. 132፥7። ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥
ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መርገጫ ስገዱ።
6 #
ኤር. 15፥1። ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥
ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው፥
ጌታን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።
7 #
ዘፀ. 33፥9፤ ዘኍ. 12፥5። በደመና ዓምድም ተናገራቸው፥
ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።
8 #
ዘፀ. 32፥11፤ ዘኍ. 20፥12። አቤቱ አምላክችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፥
አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥
ጥፋታቸውን ሁሉ ግን ተበቀልሃቸው።
9ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥
በቅዱስ ተራራውም ስገዱ፥
ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 99: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 99
99
1 #
መዝ. 18፥8-11፤ 80፥2፤ 93፥1፤ ዘፀ. 25፥22፤ 1ሳሙ. 4፥4፤ 2ሳሙ. 6፥2። ጌታ ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፥
በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።
2ጌታ በጽዮን ታላቅ ነው፥
እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።
3 #
ኢሳ. 6፥3። ቅዱስ ነውና
ሁሉም ታላቅና ግሩም ስምህን ያመስግኑ።
4 #
መዝ. 72፥1፤ ኤር. 23፥5። ፍርድን የምትወድ ኃያል ንጉሥ፥
አንተ ቅንነትን አጸናህ፥
በያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ ፈጽምህ።
5 #
መዝ. 132፥7። ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥
ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መርገጫ ስገዱ።
6 #
ኤር. 15፥1። ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥
ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው፥
ጌታን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።
7 #
ዘፀ. 33፥9፤ ዘኍ. 12፥5። በደመና ዓምድም ተናገራቸው፥
ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።
8 #
ዘፀ. 32፥11፤ ዘኍ. 20፥12። አቤቱ አምላክችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፥
አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥
ጥፋታቸውን ሁሉ ግን ተበቀልሃቸው።
9ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥
በቅዱስ ተራራውም ስገዱ፥
ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።