መዝሙረ ዳዊት 100

100
1የምስጋና መዝሙር።
ምድር ሁሉ፥ ለጌታ እልል በሉ፥
2በደስታም ለጌታ ተገዙ፥
በእልልታም ወደ ፊቱ ግቡ።
3 # መዝ. 23፥1፤ 95፥7፤ ሚክ. 7፥14፤ ኢሳ. 64፥7። ጌታ እርሱ አምላክ እንደሆነ እወቁ፥
እርሱ ሠራን፥ እኛም የእርሱ ነን፥
እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን።
4 # መዝ. 106፥1፤ 107፥1፤ 118፥1፤ 136፥1፤ 138፥8፤ ኤር. 33፥11። ወደ ደጆቹ በውዳሴ፥
ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፥
አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፥
5ጌታ ቸር፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም፥
እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ