መዝሙረ ዳዊት 100
100
1የምስጋና መዝሙር።
ምድር ሁሉ፥ ለጌታ እልል በሉ፥
2በደስታም ለጌታ ተገዙ፥
በእልልታም ወደ ፊቱ ግቡ።
3 #
መዝ. 23፥1፤ 95፥7፤ ሚክ. 7፥14፤ ኢሳ. 64፥7። ጌታ እርሱ አምላክ እንደሆነ እወቁ፥
እርሱ ሠራን፥ እኛም የእርሱ ነን፥
እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን።
4 #
መዝ. 106፥1፤ 107፥1፤ 118፥1፤ 136፥1፤ 138፥8፤ ኤር. 33፥11። ወደ ደጆቹ በውዳሴ፥
ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፥
አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፥
5ጌታ ቸር፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም፥
እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 100: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ