መዝሙረ ዳዊት 101
101
1የዳዊት መዝሙር።
አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ።
2 #
1ነገ. 9፥4፤ መዝ. 26፥11፤ ኢሳ. 33፥15። ነቀፋ በሌለበት መንገድን እጓዛለሁ፥
ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ?
በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ።
3 #
ምሳ. 11፥20። በዓይኔ ፊት ክፉን ነገር አላኖርሁም፥
ሕግ ተላላፊዎችን ጠላሁ።
4ጠማማ ልብም ከእኔ ይርቃል፥
ክፉን አላውቀውም።
5 #
ምሳ. 17፥20፤ 21፥4፤ 30፥10። ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፥
በዓይኑ ትዕቢተኛ፥ በልቡ ኩራተኛ የሆነውን አልታገሥም።
6 #
መዝ. 26፥11፤ ምሳ. 20፥7። ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ
ዐይኖቼ በምድር ምእመናን ላይ ናቸው፥
በቀና መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል።
7 #
መዝ. 5፥5፤ ምሳ. 25፥5። አታላይ በቤቴ መካከል አይኖርም፥
ሐሰትን የሚናገር በዓይኔ ፊት አይቆምም።
8ዓመፃ የሚያደርጉትን ሁሉ ከጌታ ከተማ አጠፋቸው ዘንድ፥
የምድርን ክፉዎች ሁሉ በማለዳ አጠፋቸዋለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 101: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 101
101
1የዳዊት መዝሙር።
አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ።
2 #
1ነገ. 9፥4፤ መዝ. 26፥11፤ ኢሳ. 33፥15። ነቀፋ በሌለበት መንገድን እጓዛለሁ፥
ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ?
በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ።
3 #
ምሳ. 11፥20። በዓይኔ ፊት ክፉን ነገር አላኖርሁም፥
ሕግ ተላላፊዎችን ጠላሁ።
4ጠማማ ልብም ከእኔ ይርቃል፥
ክፉን አላውቀውም።
5 #
ምሳ. 17፥20፤ 21፥4፤ 30፥10። ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፥
በዓይኑ ትዕቢተኛ፥ በልቡ ኩራተኛ የሆነውን አልታገሥም።
6 #
መዝ. 26፥11፤ ምሳ. 20፥7። ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ
ዐይኖቼ በምድር ምእመናን ላይ ናቸው፥
በቀና መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል።
7 #
መዝ. 5፥5፤ ምሳ. 25፥5። አታላይ በቤቴ መካከል አይኖርም፥
ሐሰትን የሚናገር በዓይኔ ፊት አይቆምም።
8ዓመፃ የሚያደርጉትን ሁሉ ከጌታ ከተማ አጠፋቸው ዘንድ፥
የምድርን ክፉዎች ሁሉ በማለዳ አጠፋቸዋለሁ።