የዮሐንስ ራእይ መግቢያ
መግቢያ
የዮሐንስ ራእይ የተጻፈው ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታቸው መሆኑን በማመናቸው ምክንያት ስደትና መከራ ይደርስባቸው በነበረ ጊዜ ነው። የጸሐፊው ዋና ትኲረት አንባቢዎቹ በተስፋ እንዲሞሉ ለማበረታታትና በደረሰባቸው ስደትና መከራ ውስጥ በእምነታቸው እንዲጸኑ ለማደፋፈር ነው።
የዮሐንስ ራእይ በሁለት ዐበይት ክፍሎች የተዋቀረ ነው። በመጀመሪያው ክፍል ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት የተላኩ የጥበብ መልእክቶችን እናገኛለን፤ እነኚህም የመጽሐፉን የመጀመሪያ ሦስት ምዕራፎች ያካትታሉ። ከምዕራፍ አራት እስከ መጨረሻው ድረስ ያለውን ክፍል ለመከታተል የሰባት ማኅተሞችን፥ የሰባት መለኮቶችንና የሰባት ጽዋዎችን ትእይንት ማስተዋል ያስፈልጋል።
የመጽሐፉ አብዛኛው ክፍል ብዛት ያላቸውና ተከታታይ የሆኑ ራእዮችን የያዘ ነው፤ ራእዮቹም በዚያን ዘመን የነበሩ ምእመናን ሊረዱአቸው የሚችሉ፥ ለሌሎች ግን ምሥጢር ሆነው የሚቈዩ ሲሆን በሥዕላዊ አነጋገር የቀረቡ ናቸው። የመዝሙር አዝማች እንደሚደጋገመው ዓይነት የዚህም መጽሐፍ ርእሶች በተለያዩት ራእዮች አማካይነት በተለያየ መልክ ተደጋግመው ቀርበዋል። ስለ መጽሐፉ አተረጓጐም የተለያየ ሐሳብ ያለ ቢሆንም ዋናው ሐሳብ ግልጥ ነው፤ ይኸውም እግዚአብሔር፥ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በማያዳግም ሁኔታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ፥ ሰይጣንን ጭምር፥ ጠላቶቹን ሁሉ ድል ነሥቷል፤ የድሉ ሙላት በሚከበርበት ጊዜ ታማኝ ለሆኑ ወገኖቹ የአዲስ ሰማይንና የአዲስ ምድርን በረከት ያወርሳቸዋል የሚለው ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-8)
የራእዩ መክፈቻና ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያን የተላከ መልእክት (1፥9—3፥22)
መጽሐፉና ሰባቱ ማኅተሞች (4፥1—8፥1)
ሰባቱ መለከቶች (8፥2—11፥19)
ዘንዶውና ሁለቱ እንስሶች (12፥1—13፥18)
የተለያዩ ራእዮች (14፥1—15፥8)
ሰባቱ የእግዚአብሔር ቊጣ ጽዋዎች (16፥1-21)
የባቢሎን ጥፋት፥ የአውሬው፥ የሐሰተኛው ነቢይና የዲያብሎስ መሸነፍ (17፥1—20፥10)
የመጨረሻው ፍርድ (20፥11-15)
አዲስ ሰማይ፥ አዲሲቱ ምድር፥ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም (21፥1—22፥5)
ማጠቃለያ (22፥6-21)
ምዕራፍ
Currently Selected:
የዮሐንስ ራእይ መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ