መኃልየ መኃልይ 3
3
1ሌሊት በመኝታዬ ላይ
ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፥
ፈለግሁት አላገኘሁትም።
2እነሣለሁ በከተማይቱም እዞራለሁ፥
ነፍሴ የወደደችውን
በጎዳናና በአደባባይ እፈልጋለሁ፥
ፈለግሁት አላገኘሁትም።
3ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥
ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? አልኋቸውም።
4ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ
ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም
ወደ እናቴም ቤት ወደ ወለደችኝም እልፍኝ
እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።
5እናንተ የኢየሩሳሌም ቈንጃጅት ሆይ፥
እርሱ እስኪፈልግ ድረስ፥
ፍቅርን እንዳታስነሡትና እንዳታነሣሡት
በሚዳቋ በምድረ በዳም ዋላ አስምላችኋለሁ።
6መዓዛም እንደ ከርቤና እንደ ዕጣን የሆነችው፥
ከልዩ ከነጋዴ ቅመም ሁሉ የሆነችው፥
ይህች ከምድረበዳ እንደ ጢስ ምስሶ የወጣችው ማን ናት?
7እነሆ፥ የሰሎሞን አልጋ ናት፥
ከእስራኤል ኃያላን መካከል ስድሳ ኃያላን በዙሪያው ናቸው።
8ሁሉም ሰይፍ የያዙና ጦርነት የለመዱ ናቸው፥
በሌሊት ከሚከሰት አደጋ የተነሣ
ሰው ሁሉ ሰይፉ በወገቡ አለ።
9ንጉሡ ሰሎሞን መቀመጫ
ከሊባኖስ እንጨት ለራሱ አሠራ።
10ምሰሶቹን የብር፥ መደገፊያውንም የወርቅ፥
መቀመጫውንም ሐምራዊ ግምጃ አደረገ፥
ውስጡ በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ፍቅር የተለበጠ ነው።
11እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት፥ ውጡ፥
እናቱ በሰርጉ ቀንና በልቡ ደስታ ቀን ያደረገችለትን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን እዩ።
Currently Selected:
መኃልየ መኃልይ 3: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ