የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መኃልየ መኃልይ 4

4
1ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥
እነሆ፥ አንቺ ወብ ነሽ፥
ዐይኖችሽ በመሸፈኛሽ#4፥1 ሴቲቱ ፊቷን የተሸፈነችበት ዓይነ ርግብ ወይም ውጭውን የሚያሳይ ስስ ጨርቅ። ውስጥ ርግቦች ናቸው#4፥1 ርግብ የዋህ፥ ውብና የማትጎዳ እንደ ሆነች ሁሉ።
ጠጉርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ
እንደ ፍየል መንጋ ነው።
2ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ተሸለቱ
ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ
ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው#4፥2 ጥርሶችሽ ነጫጭና፥ ውብ ናቸው።
3ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥
አፍሽም ያማረ ነው፥
በመሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭና ጉንጭሽ
እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።
4አንገትሽ ለጦር ዕቃ መስቀያ እንደ ተሠራው እንደ ዳዊት ግንብ ነው፥
ሺህ ጋሻ የኃያላንም መሣሪያ ሁሉ ተንጠልጥሎበታል።
5ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ እንደ ተወለዱ፥
በሱፍ አበባ መካከል እንደሚሰማሩ
እንደ ሚዳቋ ግልገሎች ናቸው።
6ቀኑ እስኪነፍስ ጥላውም እስኪያልፍ ድረስ፥
ወደ ከርቤው ተራራ ወደ ዕጣኑም ኮረብታ እሄዳለሁ።
7ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥
ነውርም የለብሽም።
8ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥
ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥
ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥
ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።
9እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፥
አንድ ጊዜ በዐይኖችሽ፥ ከአንገትሽስ ድሪ በአንዱ
ልቤን በደስታ አሳበድሽው።
10እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው!
ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል!
የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ! 11ሙሽራዬ ሆይ፥ ከከንፈሮችሽ ማር ይንጠበጠባል፥
ከምላስሽ በታች ማርና ወተት አለ፥
የልብስሽም መዓዛ እንደ ሊባኖስ መዓዛ ነው።
12እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥
የተቈለፈ ገነት፥ የታተመም ምንጭ ናት።
13ቡቃያሽ ሮማንና የተመረጠ ፍሬ፥
ዕፀ ሕና#4፥13 እንሶስላ። ከናርዶስ#4፥13 ናርዶስ ቅመም ነው። ጋር ያለበት ገነት ነው፥
14ናርዶስ ከቀጋ ጋር፥ የሽቱ ሣርና ቀረፋ፥
ከልዩ ልዩ የዕጣን ዕፀዋት ጋር፥
ከርቤና እሬት ከምርጥ ቅመሞች ሁሉ ጋር።
15የገነት ምንጭ፥ የሕይወት ውኃ ጉድጓድ፥
ከሊባኖስም የሚፈስሱ ወንዞች።
16የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥
የደቡብም ነፋስ ና፥
በገነቴ ላይ ንፈስ፥
ሽቱውም ይፍሰስ፥
ውዴ ወደ ገነቱ ይግባ
ምርጡንም ፍሬ ይብላ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ