መኃልየ መኃልይ 6

6
1ውድሽ ወዴት ሄደ? አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፥
ከአንቺ ጋር እንፈልገው ውድሽ ወዴት ፈቀቅ አለ?
2ውዴ በገነቱ መንጋውን ያሰማራ ዘንድ
አበባውንም ይሰበስብ ዘንድ
ወደ ሽቱ መደብ ወደ ገነቱ ወረደ።
3እኔ የውዴ ውዴም የእኔ ነው፥
በሱፉ አበባ መካከል መንጋውን ያሰማራል።
4ወዳጄ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ውብ ነሽ፥
እንደ ኢየሩሳሌምም ያማርሽ ነሽ፥
ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት ታስፈሪያለሽ።
5አውከውኛልና ዐይኖችሽን ከፊቴ መልሺ፥
ጠጉርሽ ከገለዓድ እንደ ወረደ እንደ ፍየል መንጋ ነው።
6ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ወጡ
ሁሉ መንታ እንደ ወለዱ
ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው።
7በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭና ጉንጭሽ
እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።
8ስልሳ ንግሥቶች ሰማንያም ቁባቶች
ቍጥር የሌላቸውም ቈነጃጅት አሉ።
9ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ አንዲት ናት፥
ለእናትዋ አንዲት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት።
ቈነጃጅትም አይተው ብፅዕት አሉአት፥
ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኑአት።
10ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥
እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች፥
ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት?
11የወንዙን ዳር ልምላሜ አይ ዘንድ፥
ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደሆነ እመለከት ዘንድ
ወደ ለውዝ ገነት ወረድሁ።
12ሳላውቅ ነፍሴ በከበረው ሠረገላ#6፥12 “በከበረው ሐዝቤ” ወይም በአሚናዳብ ሠረገላ ብለው የሚተረጉሙ አሉ። ላይ አስቀመጠችኝ።
13አንቺ ሱላማጢስ ሆይ። ተመለሽ፥ ተመለሽ፥
እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ።
በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ?
እርሷ እንደ መሃናይም#6፥13 የቦታ ስም። ዘፈን ናት።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ