መኃልየ መኃልይ 7
7
1አንቺ ልዕልት ሆይ፥
እግሮችሽ በነጠላ ጫማ ውስጥ እንዴት ውብ ናቸው!
ዳሌዎችሽስ በአንጥረኛ እጅ እንደ ተሠሩ
እንደ ዕንቁዎች ይመስላሉ።
2እንብርትሽ የወይን ጠጅ እንደማይጐድልበት
እንደ ተነጠጠ ጽዋ ነው፥
ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር፥ በአበባም እንደ ታጠረ ነው።
3ሁለቱ ጡቶችሽ እንደ ሁለቱ መንታ
እንደ ሚዳቋ ግለገሎች ናቸው።
4አንገትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው፥
ዐይኖችሽ በሐሴቦን#7፥4 ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ቀኝ የሚገኝ የቦታ ስም። ውስጥ በባትረቢ በር አጠገብ
የሚግኙ ኩሬዎች ናቸው፥ #7፥4 በኩሬ ውሰጥ በሚግኝ ውሃ ላይ ብርሃን ያንጸባርቃል፤ በዕብራይስጥ ቋንቋ ዐይንና ኩሬ ተመሳሳይ ፊደል አላቸው።
አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ እንደሚመለከት
እንደ ሊባኖስ ግንብ ነው#7፥4 ረጅምና ቀጥ ያለ አፍንጫን ለማመልከት የቀረበ ምሳሌ።።
5ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ በላይሽ ነው፥
የራስሽም ጠጉር እንደ ሐምራዊ ሐር ነው፥
ንጉሡ በሹርባው ታስሮአል።
6ፍቅር ሆይ፥ እንዴት የተዋብሽ ነሽ!
እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ! በተድላ
7ይህ ቁመትሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥
ጡቶችሽም አስካሉን ይመስላሉ።
8ወደ ዘንባባው ዛፍ እወጣለሁ
ጫፎችዋንም እይዛለሁ አልሁ፥
ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ
የአፍንጫሽም ሽቱ እንደ እንኮይ ናቸው።
9አፍሽ ለወዳጄ እየጣፈጠ እንደሚገባ፥
የተኙትን ከንፈሮች ይናገሩ ዘንድ እንደሚያደርግ፥
እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ነው።
10እኔ የውዴ ነኝ፥ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው።
11ውዴ ሆይ፥ ና፥ ወደ መስክ እንውጣ በመንደሮችም እንደር።
12ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፥
ወይኑ አብቦ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ
ሮማኑም አፍርቶ እንደሆነ እንይ፥
በዚያ ፍቅሬን እሰጥሃለሁ።
13ትርንጎዎች መዓዛን ሰጡ፥
መልካሞች ፍሬዎች ሁሉ፥
አሮጌው ከአዲሱ#7፥13 የበሰለውና ሊበስል ያለው። ጋር፥ በደጃችን አሉ፥
ውዴ ሆይ፥ ሁሉን ለአንተ ጠበቅሁልህ።
Currently Selected:
መኃልየ መኃልይ 7: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ