ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 13:1-7

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 13:1-7 አማ2000

የሰ​ውን ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ የመ​ላ​እ​ክ​ት​ንም ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌ​ለኝ እን​ደ​ሚ​ጮህ ነሐስ፥ ወይም እን​ደ​ሚ​መታ ከበሮ መሆኔ ነው። ትን​ቢት ብና​ገር፥ የተ​ሰ​ው​ረ​ውን ሁሉ፥ ጥበ​ብ​ንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍ​ለስ የሚ​ያ​ደ​ርስ ፍጹም እም​ነ​ትም ቢኖ​ረኝ ፍቅር ከሌ​ለኝ ከንቱ ነኝ። ገን​ዘ​ቤን ሁሉ ለም​ጽ​ዋት ብሰጥ፥ ሥጋ​ዬ​ንም ለእ​ሳት መቃ​ጠል ብሰጥ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌ​ለኝ ምንም አይ​ጠ​ቅ​መ​ኝም። ፍቅር ያስ​ታ​ግ​ሣል፤ ፍቅር ያስ​ተ​ዛ​ዝ​ናል፤ ፍቅር አያ​ቀ​ና​ናም፤ ፍቅር አያ​ስ​መ​ካም፤ ፍቅር ልቡ​ናን አያ​ስ​ታ​ብ​ይም። ብቻ​ዬን ይድ​ላኝ አያ​ሰ​ኝም፤ አያ​በ​ሳ​ጭም፤ ክፉ ነገ​ር​ንም አያ​ሳ​ስ​ብም። ጽድ​ቅን በመ​ሥ​ራት ደስ ያሰ​ኛል እንጂ፥ ግፍን በመ​ሥ​ራት ደስ አያ​ሰ​ኝም። በሁሉ ያቻ​ች​ላል፤ በሁ​ሉም ያስ​ተ​ማ​ም​ናል፤ በሁ​ሉም ተስፋ ያስ​ደ​ር​ጋል፥ በሁ​ሉም ያስ​ታ​ግ​ሣል።