የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 16

16
ዳዊት ለመ​ን​ገሥ እንደ ተቀባ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ ለና​ቅ​ሁት ለሳ​ኦል የም​ታ​ለ​ቅ​ስ​ለት እስከ መቼ ነው? የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ሞል​ተህ ና፤ በል​ጆቹ መካ​ከል ለእኔ ንጉሥ አዘ​ጋ​ጅ​ቼ​አ​ለ​ሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እል​ክ​ሃ​ለሁ” አለው። 2ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እን​ዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገ​ድ​ለ​ኛል” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አን​ዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ‘ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ’ በል። 3እሴ​ይ​ንም ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ጥራው፥ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም አስ​ታ​ው​ቅ​ሃ​ለሁ፤ የም​ነ​ግ​ር​ህ​ንም ቅባው” አለው። 4ሳሙ​ኤ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን አደ​ረገ፤ ወደ ቤተ ልሔ​ምም መጣ። የከ​ተ​ማ​ውም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በተ​ገ​ና​ኙት ጊዜ ደነ​ገጡ፥ “ነቢይ! የመ​ጣ​ኸው ለሰ​ላም ነውን?” አሉት። 5እር​ሱም፥ “ለሰ​ላም ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ፤ ቅዱ​ሳን ሁኑ፤ ከእ​ኔም ጋር ዛሬ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ኔም ጋር ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ኑ” አለ። እሴ​ይ​ንና ልጆ​ቹ​ንም ቀደ​ሳ​ቸው፤ ወደ መሥ​ዋ​ዕ​ቱም ጠራ​ቸው።
6እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤል​ያብ ተመ​ል​ክቶ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ባው በፊቱ ነው” አለ። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው። 8እሴ​ይም አሚ​ና​ዳ​ብን ጠርቶ በሳ​ሙ​ኤል ፊት አሳ​ለ​ፈው፤ እር​ሱም፥ “ይህን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ረ​ጠ​ውም” አለ። 9እሴ​ይም ሣማ​ዕን አሳ​ለ​ፈው፤ እር​ሱም፥ “ይህን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ረ​ጠ​ውም” አለ። 10እሴ​ይም ከል​ጆቹ ሰባ​ቱን በሳ​ሙ​ኤል ፊት አሳ​ለ​ፋ​ቸው። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አል​መ​ረ​ጠም” አለው። 11ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “ልጆ​ችህ እኒህ ብቻ ናቸው?” አለው። እር​ሱም፥ “ታናሹ ገና ቀር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በጎ​ችን ይጠ​ብ​ቃል” አለ። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እርሱ እስ​ኪ​መጣ ድረስ ለማ​ዕድ አን​ቀ​መ​ጥ​ምና ልከህ አስ​መ​ጣው” አለው። 12ልኮም አስ​መ​ጣው፤ እር​ሱም ቀይ፥ ዐይ​ኑም የተ​ዋበ፥ መል​ኩም ያማረ ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ይህ መል​ካም ነውና ተነ​ሥ​ተህ ዳዊ​ትን ቅባው” አለው። 13ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቀባው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳ​ዊት ላይ መጣ። ሳሙ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ወደ አር​ማ​ቴም ሄደ።
14የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከሳ​ኦል ራቀ፤ ክፉም መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀው። 15የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች፥ “እነሆ፥ ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያስ​ጨ​ን​ቅ​ሃል፤ 16አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በፊ​ትህ ይና​ገሩ፤ በበ​ገና የሚ​ዘ​ምር ሰውም ለጌ​ታ​ቸው ይፈ​ል​ጉ​ለት፤ ክፉ መን​ፈ​ስም በመ​ጣ​ብህ ጊዜ በገ​ና​ውን ሲመታ አንተ ደኅና ትሆ​ና​ለህ፤ እር​ሱም ያሳ​ር​ፍ​ሃል” አሉት። 17ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “መል​ካም አድ​ርጎ በገና መም​ታት የሚ​ችል ሰው ፈል​ጋ​ችሁ አም​ጡ​ልኝ” አላ​ቸው። 18ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መል​ካም አድ​ርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔ​ሙን የእ​ሴ​ይን ልጅ አይ​ቻ​ለሁ፤ ሰው​የ​ውም ጠቢብ፥ ተዋ​ጊም ነው፤ በነ​ገ​ርም ብልህ፥ መል​ኩም ያማረ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነው” አለ። 19ሳኦ​ልም ወደ እሴይ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ፥ “ከመ​ን​ጋ​ዎ​ችህ ጋር ያለ​ውን ልጅ​ህን ዳዊ​ትን ላክ​ልኝ” አለ። 20እሴ​ይም እን​ጀ​ራና የወ​ይን ጠጅ አቁ​ማዳ የተ​ጫነ አህያ፥ አን​ድም የፍ​የል ጠቦት ወስዶ በልጁ በዳ​ዊት እጅ ወደ ሳኦል ላከ። 21ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል መጣ፤ በፊ​ቱም ቆመ፤ እጅ​ግም ወደ​ደው፤ ለእ​ር​ሱም ጋሻ ጃግ​ሬው ሆነ። 22ሳኦ​ልም ወደ እሴይ፥ “በዐ​ይኔ ሞገስ አግ​ኝ​ቶ​አ​ልና ዳዊት በፊቴ እባ​ክህ ይቁም፥” ብሎ ላከ። 23እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ያ ክፉ መን​ፈስ በሳ​ኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦ​ል​ንም ደስ ያሰ​ኘው፥ ያሳ​ር​ፈ​ውም ነበር፥ ክፉው መን​ፈ​ስም ከእ​ርሱ ይርቅ ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ