የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 22

22
ሳኦል ካህ​ና​ትን እንደ ገደለ
1ዳዊ​ትም ከዚያ ተነ​ሥቶ አመ​ለጠ፤ ወደ ዔዶ​ላም ዋሻም መጣ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹና የአ​ባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ወደ​ዚያ ወረዱ። 2የተ​ጨ​ነ​ቀም ሁሉ፥ ዕዳም ያለ​በት ሁሉ፥ የተ​ከ​ፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​ባ​ሰበ፤ እር​ሱም በላ​ያ​ቸው አለቃ ሆነ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።
3ዳዊ​ትም ከዚያ በሞ​ዓብ ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ መሴፋ ሄደ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም ንጉሥ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ል​ኝን እስ​ካ​ውቅ ድረስ አባ​ቴና እናቴ ከአ​ንተ ጋር ይቀ​መጡ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው። 4የሞ​ዓ​ብ​ንም ንጉሥ ማለ​ደው፤ ዳዊ​ትም በአ​ንባ ውስጥ በነ​በ​ረ​በት ወራት ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ ተቀ​መጡ። 5ነቢዩ ጋድም ዳዊ​ትን፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ እንጂ በአ​ን​ባው ውስጥ አት​ቀ​መጥ” አለው፤ ዳዊ​ትም ሄደ፤ ወደ ሳሬቅ ከተ​ማም መጥቶ ተቀ​መጠ፤
6ሳኦ​ልም ዳዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሰዎች ያሉ​በት ቦታ እንደ ታወቀ ሰማ። ሳኦ​ልም በራማ በሚ​ገ​ኘው በመ​ሰ​ማ​ር​ያው ቦታ በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ተቀ​ምጦ በእ​ጁም ጦር ይዞ ነበር፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ሁሉ በአ​ጠ​ገቡ ቆመው ነበር። 7ሳኦ​ልም በአ​ጠ​ገቡ የቆ​ሙ​ትን ብላ​ቴ​ኖች፥ “ብን​ያ​ማ​ው​ያን ሆይ! እን​ግ​ዲህ ስሙ በእ​ው​ነት የእ​ሴይ ልጅ እር​ሻና የወ​ይን ቦታ ለሁ​ላ​ችሁ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልን? ሁላ​ች​ሁ​ንስ መቶ አለ​ቆ​ችና ሻለ​ቆች ያደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልን? 8ሁላ​ችሁ በላዬ ዶል​ታ​ችሁ ተነ​ሣ​ች​ሁ​ብኝ፤ ልጄ ከእ​ሴይ ልጅ ጋር ሲማ​ማል ማንም አል​ገ​ለ​ጠ​ል​ኝም፤ ከእ​ና​ን​ተም አንድ ለእኔ የሚ​ያ​ዝን የለም፤ ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ልጄ አገ​ል​ጋ​ዬን እን​ዲ​ዶ​ልት ሲያ​ስ​ነ​ሣ​ብኝ ማንም አላ​ስ​ታ​ወ​ቀ​ኝም” አላ​ቸው። 9የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ መልሶ፥ “የእ​ሴይ ልጅ ወደ ኖብ ወደ አኪ​ጦብ ልጅ ወደ ካህኑ አቤ​ሜ​ሌክ ሲመጣ አይቼ​ዋ​ለሁ። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጠየ​ቀ​ለት፤ ስን​ቅ​ንም ሰጠው፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም የጎ​ል​ያ​ድን ሰይፍ ሰጠው” አለው።
11ንጉ​ሡም የአ​ኪ​ጦ​ብን ልጅ ካህ​ኑን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ በኖ​ብም ያሉ​ትን ካህ​ናት፥ የአ​ባ​ቱን ልጆች ሁሉ ልኮ አስ​ጠ​ራ​ቸው፤ ሁላ​ቸ​ውም ወደ ንጉሡ መጡ። 12ሳኦ​ልም፥ “የአ​ኪ​ጦብ ልጅ ሆይ! እን​ግ​ዲህ ስማ” አለ፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ ጌታዬ ሆይ” ብሎ መለሰ። 13ሳኦ​ልም፥ “አንተ ከእ​ሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለ​ት​ህ​ብኝ? እን​ጀ​ራና ሰይፍ ሰጠ​ኸው፤ ዛሬም እንደ ተደ​ረ​ገው ጠላት ሆኖ ይነ​ሣ​ብኝ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ እርሱ ጠየ​ቅ​ህ​ለት” አለው። 14አቤ​ሜ​ሌ​ክም መልሶ ንጉ​ሡን፥ “ከባ​ሪ​ያ​ዎቹ ሁሉ የታ​መነ፥ ለን​ጉ​ሥም አማች የሆነ፥ የት​እ​ዛ​ዝህ ሁሉ አለቃ፥ በቤ​ት​ህም የከ​በረ እንደ ዳዊት ያለ ማን ነው? 15በውኑ ስለ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመ​ር​ሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ይህን ሁሉ ትልቅ ወይም ጥቂት ቢሆን አላ​ው​ቅ​ምና ንጉሡ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ነገር በእኔ በባ​ሪ​ያ​ውና በአ​ባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያ​ኑር” አለ። 16ንጉ​ሡም፥ “አቤ​ሜ​ሌክ ሆይ! አን​ተና የአ​ባ​ትህ ቤት ሁሉ ፈጽ​ማ​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ” አለ። 17ንጉ​ሡም በዙ​ሪ​ያው የቆ​ሙ​ትን እግ​ረ​ኞች፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት እጅ ከዳ​ዊት ጋር ነውና፥ ኵብ​ለ​ላ​ው​ንም ሲያ​ውቁ አል​ነ​ገ​ሩ​ኝ​ምና፥ ዞራ​ችሁ ግደ​ሉ​አ​ቸው” አላ​ቸው። የን​ጉሡ አገ​ል​ጋ​ዮች ግን እጃ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት ላይ ይዘ​ረጉ ዘንድ እንቢ አሉ። 18ንጉ​ሡም ዶይ​ቅን፥ “አንተ ዞረህ ካህ​ና​ቱን ግደ​ላ​ቸው” አለው። ሶር​ያ​ዊው ዶይ​ቅም ዞሮ ካህ​ና​ቱን ገደ​ላ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀን የበ​ፍታ ኤፉድ የለ​በ​ሱ​ትን ሦስት መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሦስት መቶ አም​ስት” ሲል ዕብ. “ሰማ​ንያ አም​ስት” ይላል። ሰዎ​ችን ገደለ። 19የካ​ህ​ና​ቱ​ንም ከተማ ኖብን በሰ​ይፍ ስለት መታ፤ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ች​ንም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ንና ጡት የሚ​ጠ​ቡ​ትን፥ በሬ​ዎ​ች​ንና አህ​ዮ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደለ።
20ከአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጆች ስሙ አብ​ያ​ታር የሚ​ባል አንዱ ልጅ አም​ልጦ ሸሸ፤ ዳዊ​ት​ንም ተከ​ተለ። 21አብ​ያ​ታ​ርም ሳኦል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ካህ​ናት እንደ ፈጀ ለዳ​ዊት ነገ​ረው። 22ዳዊት አብ​ያ​ታ​ርን፦ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ በዚያ መኖ​ሩን ባየሁ ጊዜ፥ “ለሳ​ኦል በር​ግጥ ይነ​ግ​ራል ብዬ በዚያ ቀን አው​ቄ​ዋ​ለሁ፤ ለአ​ባ​ትህ ቤት ነፍስ ሁሉ ጥፋት በደ​ለ​ኛው እኔ ነኝ። 23እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ፤ አት​ፍራ፤ ለእኔ ነፍስ የደ​ኅ​ን​ነት ቦታን እን​ደ​ም​ፈ​ልግ ለአ​ን​ተም ነፍስ የደ​ኅ​ን​ነት ቦታን እፈ​ል​ጋ​ለ​ሁና፥ ከእ​ኔም ጋር ተጠ​ብ​ቀህ ትኖ​ራ​ለህ” አለው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ